Friday, January 24, 2025

ለግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ መስፈርት ለማሳወቅ የወጣ ማስታወቂያ
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ታህሳስ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ፒያሳ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ የስብሰባ አዳራሽ በሚያካሂደው 11ኛ የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫን ያካሂዳል፡፡
በመሆኑም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/91/2024 አንቀጽ 9(3) መሠረት የጥቆማና ምርጫ መስፈርት ምርጫው ከሚካሄድበት ቀን አንድ ወር በፊት ለባለአክሲዮኖች መገለጽ እንዳለበት በሚደነግገው አግባብ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ዕጩዎችን በስብሰባው ዕለት መጠቆምና መምረጥ እንድትችሉ ለመላው የባንካችን ባለአክሲዮኖች ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

Related Stories