በኢፌዲሪ ንግድ ሕግ አንቀጽ 366 (1)፣ 367 (1 እና 2)፣ አንቀጽ 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማኀበሩ መመሥረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 14 (1) መሠረት የሕብረት ባንክ አ.ማ. የባለአክስዮኖች 27ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ሐሙስ፣ ሕዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ ካዛንችስ በሚገኘው ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ስለሚያካሂድ፣ የባንኩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በስብሰባው ላይ እንዲገኙ የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
