የንስር ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እና 4ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ቅዳሜ፤ ህዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የአክስዮን ማኅበሩ ባለአክሲዮኖች በተጠቀሰው ቀንና ቦታ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያስተላልፋል፡፡ማኅበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎችየአክስዮን ማኅበሩ ስም ንስር ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ. የአክስዮን ማኅበሩ ዓይነት በአነስተኛ የፋይናንስ ሥራ ላይ የተሰማራ የአክስዮን ማኅበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ ብር 521,537,000.00 የአክስዮን ማኅበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ ብር 521,537,000.00 የአክስዮን ማኅበሩ የምዝገባ ቁጥር MT/AA/3/0026952/2006የአክስዮን ማኅበሩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ አዲስ አበባ፤ ቦሌ ክ/ከ ፤ ወረዳ 03፤ የቤት ቁ.084የ12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎችየጉባዔውን አጀንዳዎች ማፅደቅ፤አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል እና የአክሲዮኖችን ግዢ እና ዝውውሮች ማፅደቅ፤የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርትን ማዳመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ፤የውጭ ኦዲተሮች ዓመታዊ ሪፖርትን ማዳመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ፤እ.ኤ.አ የ2024/2025 በጀት ዓመት የትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ተወያይቶ ማፅደቅ፤የጉባዔውን ቃለ ጉባኤ በንባብ ማሰማትና ማፅደቅ፤የ4ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎችየጉባዔውን አጀንዳዎች ማፅደቅ፤የማህበሩን የመመሥረቻ ፅሁፉን ማሻሻል እና ማጽደቅ፤የጉባዔውን ቃለ ጉባኤ በንባብ ማሰማትና ማፅደቅ፤ማሳሰቢያ ባለአክሲዮኖች በስብሰባው ላይ ለመገኘት ማንነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ፤ ብሔራዊ መታወቂያ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ይዞ መቅረብ አለበት፡፡ በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ በተሰጠ ውክልና ወይም በንግድ ሕጉ አንቀፅ 377 መሰረት ጉባኤው ከሚካሄድበት ቀን 3 /ሶስት/ ቀናት በፊት ቦሌ መንገድ ከሩዋንዳ መገንጠያ ወደ አትላስ በሚወስደው መንገደ 300 ሜትር ርቀት በቀኝ በኩል በሚገኘው የማኅበሩ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ 4ኛ ፎቅ የማኅበሩ የአክሲዮን ክፍል ማንነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ፤ ብሔራዊ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት በመቅረብ የውክልና መስጫ ቅፅ መሙላት ይችላሉ፡፡አንድ ባአክሲዮን በአክሲዮን ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም በስራ ላይ ያሉ የአክሲዮን ማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እና ሠራተኞች ባለአክሲዮኖችን በመወከል በብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/91/2024 አንቀፅ 20.3 መሰረት በጉባኤው ላይ መሳተፍ የማይችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ ባለአክሲዮኖች በስልክ ቁጥር 0115 622225/0115 622668 ወይንም በ 0913340442 በመደወል ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡ የንስር ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ


