እነሆ ለድፍን ሦስት አሥርት ዓመታት ቃላችንን ጠብቀን፤ አለኝታዎን አስከብረን፤ የደንበኞቻችንን የአእምሮ ሰላም አስፍነን፤ 30 ማርች ስምንቶችን አሳለፍን፡፡
- 30 የሥኬ ና የብርታት ዓመታት፤
- 30 የታማኝነትና የቅን አገልግሎት ዓመታት፤
- 30 የጥንካሬና የአለኝታዎ ዓመታት፤
30 ዓመታት አብራችሁን ለተጓዛችሁ፤ የዕድገታችን መሠረት፤ የስኬታችን ማማ፤ የጥንካሬያችን ብርታት ለሆናችሁ ሁሉ ክብር ለእናንተ ይሁን፡፡
ክብር ለደንበኞቻችን፤
ኩባንያችን የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመቱን እየዘከረ ባለበት በዚህ ወቅት ልክ እንደ አለፉት ዓመታት ሁሉ ለማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በልዩ ሁኔታ በተመረጡ የኢንሹራንስ ውሎች ላይ ለሴት ባለሀብቶችና ሥራ ፈጣሪዎች የ30 በመቶ የዐረቦን ክፍያ ቅናሽ ማድረጉን ሲገልጽ ደስ እያለው ነው፡፡ ፡፡
ቅናሹ ከልዩ ሽልማት ጋር የቀረበ በመሆኑ ወደ ሁሉም ደንበኞች ቤት (ቅርንጫፎች) ጎራ እያላችሁ የዕድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ በአክብሮት ጋብዘናችኋል! ቅናሹ ከየካቲት 30 ቀን 2018 ዓ. ም ጀምሮ ለሁለት ወራት ያህል ይቆያል፡፡
ክብር ለሴት እህቶቻችን፡፡
መልካም ማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን!
አለኝታዎ!
ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ.





