Tuesday, November 18, 2025

ለኒያላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የኩባንያውን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ እና ምርጫ በአስመራጭ ኮሚቴ አማካኝነት እንዲከናወን በደነገገው መሰረት የኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች ኅዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም. ባካሄዱት 30ኛ መደበኛ ስብሰባ በ2018 ዓ.ም. ለሚመረጠው ቦርድ 5 አባላት ያለው የቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ መምረጣቸው ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሰረት ኮሚቴው ዕጩ የቦርድ አባላትን ጥቆማ ከሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ብቻ የሚቀበል ስለሆነ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ SIB/32/2012 እና SIB/48/2019 ላይ የተመለከቱ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ዕጩ የቦርድ አባላትን እንድትጠቁሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

  1. የኩባንያው ባለአክሲዮን የሆነ/ች
  2. ከነባር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የአገልግሎት ዘመናቸው ያላበቃ
  3. የኩባንያው ሰራተኛ ያልሆነ
  4. እድሜው 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ/ች
  5. በሌላ የፋይናንስ ተቋም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ያልሆነ/ች
  6. የትምህርት ደረጃ፡

                ሀ) ቢያንስ 75% የሚሆኑት የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው

                ለ) የቀሩት 25% ቢያንስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ መሆን አለባቸው፡፡

  • የእምነት ማጉደል ወይም የማጭበርበር ተግባር ያልፈጸመ/ች፤ ለፋይናንሻል ተቋማትና ለተቆጣጣሪ አካል ሀሰተኛ መረጃ ያልሰጠ/ች፣ ስነ ምግባር ደንቦችን ባለማክበር የስነ-ስርአት እርመጃ ያልተወደበት/ባት፣ በሙስና ወንጀል ተከሶ ያልተፈረደበት/ባት እና ከመምረጥ መብት ያልተገደበ/ች
  • በንግድ ስራና በንግድ ስራ አስተዳደር በተለይም በኢንሹራንስ ዘርፍ የስራ ልምድ ያለው/ያላት (ቢሆን ይመረጣል)
  • በራሱ ወይም በሚመራው ወይም ዳይሬክተር በሆነበት ድርጅት ላይ የመክሰር ክስ ያልቀረበበት/ባት ወይም የኪሳራ ውሳኔ ያልተሰጠበት/ባት
  • በኪሳራ ምክንያት ንብረቱ ለእዳ ማቻቻያ ያልተወሰደበት/ባት
  • በታክስ ማጭበርበር ወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ ያልተባለ/ች
  • የሚመራው/የምትመራው ወይም ዳይሬክተር የሆነበት/የሆነችበት ድርጅት ከገንዘብ ተቋማት የተበደረውን ገንዘብ ባለመክፈሉ ብድሩ ወደ ጤናማ ያልሆነ የብድር ደረጃ ያልዞረበት/ባት
  • የባንክ ብድር ባለመክፈሉ/ሏ ምክንያት ንብረቱ/ቷ በሀራጅ ያልተሸጠ
  • ሌሎች በመመሪያዎች የተገለጹ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡

የእጩ አባላት ተጠቋሚዎች ብዛት 18 ሲሆን ከእነዘህ መካከል 1/3ኛው ማለትም 6 እጩዎች በኩባንያው ውስጥ ያላቸው የአክሲዮን ይዞታ ከ2% በታች በሆኑ ወይም ተጽእኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች የሚጠቆሙና የሚመረጡ ሲሆን ቀሪዎቹ 12ቱ ደግሞ በሁሉም ባለአክሲዮኖች የሚጠቆሙና የሚመረጡ ይሆናሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡-

በአግባቡ የተሞላውን የጥቆማ ቅጽ በቀጥታ ዋና መ/ቤት ማድረስ፣ ወይም በመ/ሳ/ቁ 12753 አዲስ አበባ ወይም በፋክስ ቁጥር 011-6-626706 ወይም በኢ-ሜይል nisco@nyalainsurance.com ወይም nisco@ethionet.et በተሰጠው የጊዜ ገደብ መላክ ይቻላል፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

Tender Notice

The Office of the United Nations High Commissioner for...

INVITATION TO BID: ETH-UNHCR -ITB-004/2025 – Managed Print Services

Closing Date: 01 December 2025, 11:59 PMFor The Establishment...

Tender Notice

The Office of the United Nations High Commissioner for...

Tender Notice

The Office of the United Nations High Commissioner for...

Acting transparently save lives

Ethiopia's swift and coordinated response to the COVID-19 pandemic...

Name: Tilahun Akililu

2. Education: (የት/ት ደረጃ)     Sport Science Degree 3. Company name: (የመስሪያ...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img