Friday, December 5, 2025

የባለአክሲዮኖች 28ኛ መደበኛ እና 15ኛ አስቸኳይ ጉባዔዎች

የስብሰባ ጥሪ

የተከበራችሁ የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ባአክሲዮኖች

በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366(1)፣ 367(1) እና አንቀጽ 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ የተሻሻለው የመመሥረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 20 መሠረት የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 28 መደበኛ እና 15 አስቸኳይ ጉባዔዎች ሐሙስ ኅዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ አዲስ አበባ ከተማ ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጠቅላላ ጉባዔዎቹ ላይ እንድትገኙልን የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 07፣ የቤ/ቁ. 351/1የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር KK/AA/2/0001775/2004የአክሲዮን ማህበሩ ዓይነት፡- በባንክ ሥራ ላይ የተሠማራ
የባንኩ ዌብ ሳይት፡- https://www.bankofabyssinia.comአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ፡- 15,000,000,000
የአክሲዮን ማህበሩ ስም፡- አቢሲንያ ባንክ አ.ማ.አክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ፡- 14,209,349,000

1.   የ28ኛው ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

1.1.      አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ፣

1.2.      የዳይሬክተሮች ቦርድን እ.ኤ.አ. የ2023/2024 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፣

1.3.       የውጭ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ. የ2023/2024 የሒሳብ ዓመት ሪፖርት ማዳመጥ፣

1.4.       በተራ ቁጥር 1.2 ላይ በቀረበው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

1.5.       በተራ ቁጥር 1.3 ላይ በቀረበው የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

1.6.      እ.ኤ.አ. በ2023/2024 የሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይ ውሳኔ መስጠት፣

1.7.      እ.ኤ.አ. የ2024/2025 የሒሳብ ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን መሾምና የአገልግሎት ክፍያቸውን መወሰን፣

1.8.       እ.ኤ.አ. የ2023/2024 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የሥራ ዋጋ ክፍያን መወሰን፣

1.9.       እ.ኤ.አ. የ2024/2025 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ የአበል ክፍያ መወሰን፣

2. የ15ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

2.1.      የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ በዳይሬክተሮች ቦርድ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

2.2.       የባንኩን የመመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻል፣

3. ማሳሰቢያ

3.1.     በጉባዔው መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻቸው ሥልጣን ባለው የመንግሥት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሠነድ ዋናውና ፎቶኮፒ በመያዝ ወይም በን/ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባዔው ከመካሄዱ ከ3 የሥራ ቀናት በፊት ለገሃር በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ አክሲዮንና ኢንቨስትመንት ክፍል ለዚሁ ዓላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባዔው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማናቸውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

3.2.     የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውና ኮፒውን በመያዝ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፤ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

   የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

Azerbaijan Builds on Victory Day to Deepen Ties with Africa at First Ethio–Azerbaijani Forum

#Advertorial Azerbaijan, fresh from celebrating the fifth anniversary of its...

Is Arsenal Finally the Team Betting Fans Can Trust This Season

Every season begins with predictions, doubts and a long...

Notice of Meeting

To All Shareholders of Shabelle Bank S.C Shabelle Bank Share...

Health Outbreaks In Reshaping The Global Economy

When a pathogen begins to spread, the first images...

Selam Ethiopia launches nationwide IP rights awareness campaign with UNESCO support

Selam Ethiopia, a leading non-governmental organization promoting arts and...

Ethiopian-American Artist Helina Metaferia Unveils ‘Syntropy’ Solo Exhibition

Ethiopian-American interdisciplinary artist Helina Metaferia opens her solo exhibition...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img