እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ለማሳወቅ የወጣ ማስታወቂያ
የብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ባለአክስዮኖች ኅዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ባካሔዱት 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የኩባንያው ባለአክስዮኖች በ2018 ዓ.ም. በሚያካሒዱት 14ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ወቅት በሚደረገው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን መልምሎ ለጉባኤው የሚያቀርብ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ መሰየሙ ይታወሳል፡፡
በዚሁ መሰረት አስመራጭ ኮሚቴው በኢትዮጵያ የንግድ ሕግና ሌሎች አግባብነት ባላቸው አዋጆች፤ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SIB/48/2019 ሌሎች አግባብነት ባላቸው መመሪያዎች፤ በኩባንያው መመስረቻ ጽሁፍ፤ እንዲሁም በኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የጥቆማ እና የምርጫ አፈጻጸም መመሪያ መሰረት ከሐምሌ 1 ቀን 2017 እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ከባለአክስዮኖች ጥቆማ በመቀበልና አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት እጩ ሆነው የቀረቡት 18 (አሥራ ስምንት) እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እና 5 (አምስት) ተጠባባቂዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ተጽዕኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክስዮኖች ብቻ ተጠቁመው ለምርጫ የቀረቡ እጩዎች
- ወ/ሮ ይመናሹ ካሳሁን መኮንን
- ወ/ሪት ትዕግስት ጌታቸው አርአያ
- ዶ/ር ተክለጻድቅ ሪባ አያኔ
- ጆሽዋ ሁለገብ ኃ/የተ/ህብረት ሥራ ማህበር (ተወካይ አቶ ኃይሌ ኑሩ ሙራረ)
- አቶ ፈለቀ ጥበበ ወ/ሰማያት
- ዶ/ር ብሩክ አየለ አሳሌ
ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ባለአክስዮኖችን ጨምሮ በሁሉም ባለአክስዮኖች ተጠቁመው ለምርጫ የቀረቡ እጩዎች
- ብርሃን ባንክ አ.ማ. (ተወካይ አቶ ኤርምያስ ተፈራ ሻውል)
- አቶ ተስፋ ታደሰ ፊዳ
- ወ/ሮ ዘውዴ በላቸው መሸሻ
- ዶ/ር ሳለሁ አንተነህ ተማረ
- አቶ አዲሱ ደምሴ ባዩ
- አቶ ዳዊት ከበደ አበራ
- አቶ ዓብይ መልካ ሮሪሳ
- አቶ መላኩ አርጋሞ ሽቱ
- ኤደን ቢዝነስ አ.ማ. (ተወካይ ዶ/ር ዝናሬ ማሞ ኃይሌ)
- ግላንስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር (ተወካይ አቶ ብርሃኑ ጌታቸው ጌንሳቶ)
- አቶ ግርማ ቦርሼ ባቲ
- ወ/ሮ ሰላማዊት ግርማ ታዬ
ተጠባባቂዎች
- አቶ ሮቤል መርሻ ጫንያለው
- ስካይ ስታንዳርድ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ተወካይ አቶ በረከት ወ/ገብርኤል ግደይ)
- አቶ በየነ ዓለሙ ወ/ማርያም
- ዶ/ር ወርቁ ኃይለማርያም መሐመድ
- አቶ ጀመራ ገመዳ መርሻ
የብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ






