Wednesday, October 7, 2026

Safaricom Ethiopia

ብቁ ድርጅቶች ፍላጎታችሁን አሳውቁን

24/7 አጠቃላይ የሕንጻ ጥገና፣ የተሟላ የቢሮ ንብረት የማጓጓዝ አገልግሎት፣ የደረቅ ቆሻሻ የማስወገድ አገልግሎት፣ የፀረ-ተባይ ቁጥጥርና ተያያዥ አገልግሎቶች ለሚሰጡ ድርጅቶች የወጣ የፍላጎት መግለጫ ማስታወቂያ (EOI)

የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን: ሰኞ, ሐምሌ 27, 2018 ዓ.ም. እስከ 11:00 ከሰዓት

  መግቢያ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙት ቢሮዎቹ፣ የአገልግሎት መስጫ ሱቆቹና መሰል መገልገያዎቹ ከታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች የሚሰጡ ብቁ፣ ልምድ ያላቸውና ችሎታ ያላቸው ድርጅቶች ፍላጎታቸውን እንዲያሳውቁት ጥሪ ያደርጋል።
ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆነ ዘርፍ ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቀ ብቁ ሆነው
የሚመረጡት ድርጅቶች ወደፊት በሚገለጽ ጊዜ ቴክኒካልና ኮመርሻል ፕሮፖዛል እንዲያስገቡ የሚደረግ ይሆናል።
የሚፈለጉ አገልግሎቶች

Lot 1 – 24/7 አጠቃላይ የሕንጻ ጥገና አገልግሎት
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለሚገለገልባቸው ሕንጻዎች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ጨምሮ አጠቃላይ የጥገና አገልግሎት አቅርቦት፡
•        ባለ ከፍተኛና ዝቅተኛ ቮልቴጅ ኤሌክትሪክ ሲስተምስ
•        ሜካኒካል ሲስተምስ
•        አሳንሰሮች
•        ጄኔሬተሮች
•        የእሳት አደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያና መከላከያዎች
•        ሲሲቲቪ እና የመግቢያ ቁጥጥር (Access Control) ሲስተሞች
•        የሕንጻ አስተዳደር ሲስተም (BMS)
•        የማሞቂያ፣ የአየር ማናፈሻና የአየር ማቀዝቀዣ (HVAC) ሲስተሞች
•        የቧንቧ ሥራ፣ ፍሳሽ አወጋገድና ሴፕቲክ ታንክ ጽዳት አገልግሎት
•        የሲቪልና አጠቃላይ ግንባታ ጥገና
•        የእንጨት ሥራዎች
•        የቀለም ቅብ ሥራዎች
•        የመብራት ሲስተሞች
•        የአስቸኳይ ጊዜ የጥገና አገልግሎት
•        በሣምንት 7 ቀን፣ በቀን 24 ሰዓት ዝግጁ የሆነ፣ ከተሟላ መገልገያ መሣሪያዎችና ቁሳቁስ ይዞ በሳፋሪኮም ሳይቶች የሚገኝ እንዲሁም በሚፈለግ ግዜ ፈጥኖ የሚሠማራ የቴክኒክ ቡድን
•        ቀድሞ መከላከልን ታሳቢ ያደረገ የጥገና ዕቅድ፣ የጥገና የጊዜ ሰሌዳ፣ የጥገና ሪፖርት ማቅረብ እና የጥገና መረጃ ሰነድ
Lot 2 – የተሟላ የቢሮ ንብረት የማጓጓዝ (ሎጂስቲክስ) አገልግሎት፣
ከታች የተዘረዘሩትን ጨምሮ የተሟላ ንብረት የማጓጓዝ አገልግሎት አቅርቦት፡
•        ቢሮ በሚቀየር ጊዜ ሙሉ ንብረት ማጓጓዝ
•        ንብረት እንዳይጎዳ ደረጃውን የጠበቀ የማሸግ (Packing) እና ማሸጊያ የማቅረብ (Packaging)t
•        ጭነት፣ ማጓጓዝ፣ ማውረድና አድርሶ ማስረከብ
•        የቢሮ ፈርኒቸርና እቃዎች መፍታት መግጠም
•        በማጓጓዝ ጊዜ የተሰባበሩ፣ የወላለቁና የተጎዱ ፈርኒቸርና አእቃዎችን እየለዩ መጠገን ማደስ
•        የተጓጓዙ ቁሳቁሶችን ቦታ ማስያዝ
•        የማይፈለጉ ማሸጊያና ሌሎች ቁሳቁስ በአግባቡ ማስወገድ
Lot 3 – የደረቅ ቆሻሻ የማስወገድ አገልግሎት፣
ከታች የተዘረዘሩትን ጨምሮ ከአካባቢ ጥበቃ መርሆዎችና ሕግጋት ጋር የሚስማማ የደረቅ ቆሻሻ አቅርቦት፡
•                   ቆሻሻ ለይቶ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል
•                   አደጋ የሌላቸው ቆሻሻዎችን ሰብስቦ ማስወገድ
•                   የቆሻሻ አሰባሰብ የጊዜ ሠሌዳ ማዘጋጀት
•                   አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቁሳቁስ አቅርቦት
•                   የኢትዮጵያን የአካባቢ ጥበቃን የተመለከቱ ሕጎችና መመሪያዎች የማክበር ግዴታ
•                   በየወቅቱ የቆሻሻ አወጋገድ ደንብ ሪፖርት ማቅረብ
Lot 4 – ፀረ-ተባይ አገልግሎት
ከታች የተዘረዘሩትን ጨምሮ የተቀናጀ የተባይ መቆጣጠሪያ አገልግሎት አቅርቦት፡
•        ተባይ መከላከልና ቁጥጥር ተግባራት
•        አይጥ ማጥፊያ
•        በረሮ ማጥፊያ
•        የወባ ትንኝና መሰል ነፍሳት ማጥፊያ
•        መደበኛ የተባይ ቁጥጥር አገልግሎት
•        አስቸኳይ የተባይ ቁጥጥር አገልግሎት
•        የተመረጡ ኬሚካሎች በአጠቃቀም መመሪያው መሠረት መጠቀም እንዲሁም ኮምፕላያንስ ሰርተፍኬት ማያያዝ
መሟላት ያለበት የፍላጎት መግለጫ ሰነዶች

ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ሰነዶች ማያያዝ አለባቸው፡
•        በተጠቀሰው ዘርፍ ለመጫረት ብቁ የሚያደርጋቸው የታደሰ የንግድ ፍቃድ
•        የንግድ ምዝገባ ምሥክር ወረቀት
•        ሕጋዊ ቲን
•        የቫት ምዝገባ ሰነድ (እንደ አስፈላጊነቱ)
•        የድርጅቱ የሚያስተዋውቅ መረጃ
•        የድርጅቱ አስተዳደራዊ መዋቅር መግለጫ
•        ድርጅቱ በዘርፉ ያካበተው የሥራ ልምድ መግለጫ
•        ድርጅቱ ባለፉት 5 ዓመታት በዘርፉ የሠራቸው 3 ሥራዎች ማስረጃ
•        ድርጅቱ እንደ ምሥክር የሚጠቅሳቸው ዋና ዋና ደንበኞች ከነአድራሻቸው
•        ድርጅቱ ያሉት ማሽነሪዎች፣ መሣሪያዎች እና ሌሎች ጠቃሚ የሥራ ቁሳቁስ በዝርዝር
•        ድርጅቱ ቀጥሮ የሚያሠራቸው ብቁ ባለሙያዎች መረጃ
•        የምሥክር ወረቀቶችና ሌሎች ድርጅቱ እውቅና ያገኘባቸው ሰነዶች (እንደ አስፈላጊነቱ)
•        የጤና፣ የደኅንነትና የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲ ሰነድ
•        የድርጅቱ የጥራት አስተዳደር መመሪያ
•        ሌሎች ጠቃሚና አጋዥ ሰነዶች

ሰነዱ የሚቀርብበት መንገድ
መጫረት የምትሹ የንግድ ድርጅቶች የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ (Expressions of Interest) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ መላክ ትችላላችሁ።
ጨረታ ማስገቢያ የኢሜይል፡ Bids@safaricom.et
የኢሜይል ርእስ (Subject)፡ EOI – Lot [Number] – [Service Name]
ለምሳሌ፡
•                   EOI – Lot 1 – 24/7 አጠቃላይ የሕንጻ ጥገና አገልግሎት
•                   EOI – Lot 2 – የተሟላ የቢሮ ንብረት የማጓጓዝ (ሎጂስቲክስ) አገልግሎት
•                   EOI – Lot 3 – የደረቅ ቆሻሻ የማስወገድ አገልግሎት፣
•                   EOI – Lot 4 – ፀረ-ተባይ አገልግሎት
ተጫራቾች ካንድ በላይ ሥራ መጫረት ይችላሉ። ሆኖም ለእያንዳንዱ ጨረታ የሚያስገቡት ፕሮፖዛል በተናጠል ኢሜይል ለየብቻ መላክ ይኖርበታል።
ለጊዜው የሚፈለገው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ብቻ ነው። በቀጣይ ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን ያለፉ ተጫራቾች ኮመርሻልና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል እንዲያስገቡ ጥሪ ይደረግላቸዋል።

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

NBE pumps extra $340M into banking system, lifting Q2 FX auctions by 68%

The National Bank of Ethiopia (NBE) has announced a...

PM Abiy confirms constitutional overhaul

Prime Minister Abiy Ahmed has officially confirmed that Ethiopia...

More Than 4,500 People Took Part in the Second Moscow Startup Summit

Startups and breakthrough technologies are transforming industries and the...

Security while Gaming: The Technologies that Keep Online Casinos Safe

Cybersecurity has become an increasingly important topic of discussion,...

Mufriat Kamil Returns to Legislative Leadership as Speaker of the House of Federation

The House of Federation (HoF) has officially elected veteran...

Africa seeks new PPP models for affordable social services

By Groum Abate African governments must improve project preparation, deepen...

Ethiopia moves to close the AfCFTA information gap with new trader guide and digital portal

Ethiopian businesses will soon have a clear, practical roadmap...
spot_img

Related Articles

Tender Notice

Popular Categories

spot_imgspot_img