Thursday, October 29, 2026

Hibret Insurance

ለተከበራችሁ የሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች፤ የ32ኛ መደበኛ እና 16ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዎች የስብሰባ ጥሪ    

በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366(1)፣ 367(1)፣ 370፣371 እና 372 እንዲሁም በአክሲዮን ማኅበሩ በተሻሻለው የመመሥረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 18 መሠረት፣ የሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 32ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 16ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ፤ ሐሙስ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ቦሌ- አፍሪካ ጎዳና ላይ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል አዳራሽ ውስጥ ስለሚካሄድ የኩባንያው ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው ላይ እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል::

      1.  አክሲዮን ማኅበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች                         

1.1. የአክሲዮን ማኅበሩ ስምሕብረት ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር
1.2. የአክሲዮን ማኅበሩ ዓይነትበመድን ሥራ ላይ የተሠማራ ኩባንያ
1.3. የአክሲዮን ማኅበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ /ካፒታል/ብር 2,000,000,000
1.4. የአክሲዮን ማኅበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ /ካፒታል/ብር 1,877,003,163.82
1.5. የአክሲዮን ማኅበሩ የምዝገባ ቁጥርMT/AA/3/0052572/2014
1.6. የአክሲዮን ማኅበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻአዲስ አበባ፣ አራዳ ክ/ከተማ፣ወረዳ 01፣ የቤት ቁጥር 220
1.7. የአክሲዮን ማኅበሩ ድረ-ገጽhttps://www.hibretinsurance.com

      2.  የባለአክሲዮኖች 32ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች      

2.1.      የመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፤

2.2.      አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ፤

2.3.      እ.ኤ.አ. የ2025/2026 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርትን ማድመጥ፤

2.4.      እ.ኤ.አ. የ2025/2026 የሒሳብ ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማድመጥ፤

2.5.      በተራ ቁጥር 2.3 ላይ በቀረበው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤

2.6.      በተራ ቁጥር 2.4 ላይ በቀረበው የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤

2.7.      እ.ኤ.አ. የ2025/2026 የሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይ በሚቀርበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤

2.8.      እ.ኤ.አ. የ2025/2026 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ዓመታዊ የሥራ ዋጋ መወሰን እና እ.ኤ.አ. የ2026/2027 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ወርሃዊ የአበል ክፍያ መወሰን፤

2.9.      የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን ምርጫ ማካሄድ እና ወርሀዊ አበላቸዉን ማስወሰን፡፡

      3.    የባለአክሲዮኖች 16ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች                

3.1.      የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፤

3.2.      የአክሲዮን ማኅበሩን የመመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻል፤

3.3.      የጉርሻ አክሲዮኖችን (Bonus Shares) በተመለከተ ተወያይቶ መወሰን፡፡

      4. ማሳሰቢያ:                                                                             

4.1. በጉባዔው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻቸው ሥልጣን ባለው የመንግሥት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሠነድ ዋናውን እና አንድ ቅጂ በመያዝ ወይም በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባዔው ከመካሄዱ ከሦስት የሥራ ቀናት በፊት ፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የሕብረት ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር ዋና መ/ቤት 9ኛ ፎቅ አክሲዮን አስተዳደር ክፍል ለዚሁ ዓላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባዔው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም፤ አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማናቸውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን፣ እንዲሁም የኩባንያው ሠራተኞች ለባለአክሲዮኖች ወኪል በመሆን በጉባዔዎቹ ላይ መሳተፍ የማይችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፤

4.2.   የአክሲዮን ማኅበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ፤ ዜግነታቸዉ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያሳይ የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ወይም የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ዋናውንና ኮፒ በመያዝ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የማኅበሩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በትህትና እያስታወቅን፤

1.3 በተጨማሪም፤ የተሻሻሉትን የመመስረቻ ጽሁፍ አንቀጾችንና ሌሎች መረጃዎችን ከድርጅቱ ድረ-ገጽ፤ https://www.hibretinsurance.com ላይ መመልከት እንደሚቻል በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡ሕብረት ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

UNHCR Representation in Ethiopia

The Office of the United Nations High Commissioner for...

SOMALI REGIONAL EDUCATION BUREAU

Invitation for Local Competitive Bidders Somali Regional Education Bureau invites...

50,000 Ethiopian refugees flood Kenyan border town as intercommunal violence flares

An estimated 50,000 people have fled renewed intercommunal violence...

Nyala insurance unveils the “NISCO Reimagined” strategy as it celebrates its 30th anniversary

​Nyala Insurance Company S.C. has reported total assets exceeding...

Ethiopia’s OTC market targets 8 securities outside main listing requirements

Ethiopia’s securities market is preparing to accommodate eight securities...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img