
የህዝብ ማስታወቂያ 13 ጥቅምት 2019
በአዲስ አበባ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) ለሰፊው ህዝብ እንደሚከተለው ማሳወቅ ይፈልጋል።
በዩኤንኤችሲአር (UNHCR) ስም የሸቀጦች እና የአገልግሎት ጨረታዎችን እያወጡ ነው በሚል ተጠርጣሪ/አጭበርባሪ የህብረተሰብ ክፍሎች የጨረታ ሰነድ እንዲገዙ ወይም በአዎንታዊ መልኩ ጥቅም ለማግኘት እና ውሉን ለመስጠት የተወሰነ የገንዘብ መጠን ለ UNHCR በሃሰተኛ የባንክ ሂሳብ ውስጥ ገንዘብ እንዲያስገቡ በመጠየቅ በአዲስ አበባ ከተማ ፡ በአካባቢው እና ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ መኖራቸውን ሰምተናል።
ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሁሉ UNHCR የማይወክሉ ወይም ለUNHCR የማይሠሩ፣ እንዲሁም UNHCR የጨረታ ሰነዱን የማይሸጥ መሆኑን፣ ማንኛውም ድርጅት ወይም የንግድ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን እንዲገዛ ወይም ማንኛውንም ገንዘብ ለUNHCR በቅድሚያ እንዲከፍል እንደማይጠይቅ ለማሳወቅ እንወዳለን። የዩኤንኤችሲአር የጨረታ ሰነዶች ከክፍያ ነፃ እና በኢትዮጵያ መንግስት የተመዘገበም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ማንኛውም በህጋዊ ለተቋቋመ አካል ክፍት ነው። UNHCR ጨረታውን ለሸቀጦች ወይም አገልግሎቶች ሲከፍት በአገር ውስጥ በሚገኙ የዜና ወረቀቶች/ጋዜጦች ላይ በግልጽ ማስታወቂያ ይወጣል እንዲሁም በ UN Global ድረ-ገጽ ላይ (UNGM.org) ይጫናል።
ስለሆነም ከላይ በተገለፀው መሰረት ህብረተሰቡ በሀሰተኛ የጨረታ ሰነድ ከሚሸጡ አጭበርባሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ UNHCR ይመክራል። UNHCR ለእንደዚህ አይነት ክስተቶች ምንም አይነት ሀላፊነት አይወስድም ። ህብረተሰቡ መሰል ጉዳዮችን ለብሄራዊ ደህንነት ቢሮዎች (ፖሊስ እና ሌሎች) ጥቆማ እንዲያደርግ ይመከራል። ከዩኤንኤችሲአር ጋር በህጋዊ መንገድ የንግድ ስራ ለመስራት ፍላጎት ያለው አካል/ኩባንያ በቀጥታ የዩኤንኤችሲአር ቢሮ እንዲያነጋግር ወይም በየጊዜው በአገር ውስጥ ጋዜጦች እና በመስመር ላይ በ UN ድህረ ገጽ ላይ በሚወጣው የጨረታ ማስታወቂያ ላይ የተሰጠውን መመሪያ እንዲከተሉ ይመከራል።
የአቅርቦት አስተዳደር አገልግሎቶች፣ የዩኤንኤችስአር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት፣ አዲስ አበባ




