Tuesday, July 8, 2025

ለብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ባለአክስዮኖች በሙሉ

እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

ኅዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም. በተካሔደው የኩባንያው ባአለክስዮኖች 13 መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጠው የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን ሲያከናውን ቆይቶ አሁን ጥቆማዎች ለመቀበል ተዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም የኩባንያው ባለአክስዮኖች ለድርጅታችን ሁለንተናዊ እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ይችላሉ ብለው የሚያምኑባቸውን ብቁ እጩዎችን ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ጥቆማዎቹን እንዲያከናውኑ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

ተጠቋሚ እጩዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርት፡

  1. የብርሃን  ኢንሹራንስ አ.ማ. ባለአክስዮን መሆን አለባቸው፡፡
  2. እድሜያቸው  ቢያንስ 30 ዓመት እና ከዛ በላይ መሆን አለበት፡፡
  3. እጩ ተጠቋሚዎቹ ቢመረጡ የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆነው ለመሥራት ፈቃደኛ ሊሆኑ ይገባል፡፡
  4. ቢያንስ 75 ከመቶ የሚሆኑት የቦርድ አባላት ከታወቀ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የሆነ የትምህርት ደረጃ  ሊኖራቸው የሚገባ ሲሆን  ቀሪዎቹ ደግሞ ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ወይም የሱን ተመጣጣኝ የሆነ ትምህርታቸውን  ያጠናቀቁ መሆን አለባቸው፡፡
  5. እጩ ተጠቋሚዎቹ በቢዝነስ ማኔጅመንት ፣ በኢንሹራንስ ሥራ በፋይናንስ፣ በአካውንቲንግ ፣ በሕግ ፣ በኦዲቲንግ ፣ በኢኮኖሚክስ ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በኢንቨስትመንት ማኔጅመንት ፣ የትምህርት መስክ የተመረቁ ፣ በንግድ ሥራ አመራር በተለይ በኢንሹራንስ የሥራ ዘርፍ ልምድ ያላቸው እና የጾታ ስብጥራቸውም ተመጣጣኝ ቢሆን ይመረጣል፡፡
  6. በብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ውስጥ በቦርድ አባልነት ቢያንስ ለስድስት ተከታታይ ዓመታት (ለሁለት የሥራ ዘመን/ተርም/ በቦርድ አባልነት ያገለገሉ ከሆነ ፣ ከቦርድ አባልነት ከለቀቁ ስድስት ዓመት የሞላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  7. እጩ ተጠቋሚዎች የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላት መሆን የለባቸውም ፡፡
  8. ሀቀኛ ፣ ታማኝ ፣ ጠንቃቃና መልካም ስነምግባር እና መልካም ዝና ያላቸው፣ በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ ዕምነት በማጉዳል ፣ በማጭበርበር  በወንጀል ተከሰው  ያልተቀጡና/ጥፋተኛ ያልተባሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጠቋሚዎቹ የብርሃን ኢንሹራንስ ፣ ሆነ የሌሎች ኢንሹራንስ ኩባንያዎች  ተቀጣሪ ሠራተኛ መሆን የሌለባቸው ሲሆን፣ በሌሎች መድን ሰጭ ተቋማትም ሆነ የፋይናንስ ተቋማት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆነው እየሠሩ መሆን የለበትም፡፡
  10. ተጠቋሚዎቹ እራሳቸው ወይም ዳይሬክተር ወይም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው በሚመሩት ድርጅት ላይ የመክሰር ክስ ያልቀረበበት ወይም የመክሰር ውሳኔ  ያልተሰጠበት መሆን አለበት፡፡
  11. ተጠቋሚዎቹ ራሳቸው ወይም ዳይሬክተር ወይም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የሚሰሩበት ድርጅት የባንክ ወይም ማንኛውንም ብድር ባለመክፈል ምክንያት ንብረታቸው በሐራጅ ያልተሸጠ፤ ተከሰው ያልተፈረደባቸው፤ ከአበዳሪ ተቋማት የወሰዱትን ገንዘብ ባለመክፈላቸው ብድሩ ወደ ጤናማ ያልሆነ ብድር የብድር ደረጃ ያልዞረባቸው ወይም ያልገባባቸው መሆን አለበት፡፡
  12. ተጠቋሚዎቹ ሥልጣን ላለው ተቆጣጣሪ አካል መስጠት ያለባቸውን መረጃ በመደበቅ& ሀሰተኛ መረጃ በመስጠት& ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት ባለማሟላት ምክንያት የእርምት እርምጃ የተወሰደባቸው መሆኑን የሚያሳይ ሪኮርድ የሌለባቸው መሆን አለበት፡፡
  13.  ተጠቋሚዎቹ በቂ ስንቅ/ገንዘብ/ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ምክንያት ሒሳባቸው ያልተዘጋባቸው/ያልተስተካከለ/ እንዲሁም ታክስ እና ግብር ባለመክፈል ተከሰው ጥፋተኛ ያልተባሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  14. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወጡ መመሪያዎች ላይ የተጠቀሱ እና ሌሎች መመዘኛዎችን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን  መስፈርት የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች  መጠቆም የምትፈልጉ ባለአክስዮኖች  ለጥቆማ የተዘጋጀውን ቅጽ/ፎርም/ ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በብርሃን  ኢንሹራንስ  አ.ማ. ድረ-ገጽ http://www.berhaninsurancesc.com ወይም የኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት ወሎ ሰፈር ጋራድ ሲቲ ሴንተር  ሕንጻ  7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 ወይንም በሁሉም የኩባንያው ቅርንጫፎች በግንባር በመቅረብ ለጥቆማ የተዘጋጀዉን ቅጽ መዉሰድ የምትችሉ መሆኑን አስመራጭ ኮሚቴው ያሳዉቃል፡፡

ባለአክሲዮኖች የሞሉትን ቅጽ በብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 በግንባር በመቅረብ መስጠት ወይም በኩባንያው የፓ.ሣ.ቁጥር 9266 ላይ አድራሻውን ለብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ በማድረግ በመላክ ወይም በኩባንያው ኢሜል BICboardnomination@berhaninsurancesc.com ሰነዱ ተሞልቶ በባለአክስዮኑ ከተፈረመ በኋላ ስካን በማድረግ ወይም ፎቶ በማንሳት በቴሌግራም ቁጥር 0997-25 99 82  አያይዘዉ መላክ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114-67 44 46/23 እና 0997-25 99 82 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከመስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት በኃላ  የሚቀርቡ ጥቆማዎችን የማይቀበል መሆኑን ኮሚቴዉ ያሳስባል፡፡

የብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ

Related Stories