Tuesday, September 15, 2026

የባለአክስዮኖች 13ኛ መደበኛ እና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤዎች የስብሰባ ጥሪ

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. የባለአክስዮኖች 13ኛ መደበኛ እና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤዎች በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1) ፣ 367(1)፣ 370፣ 371(1) እና 400 እንዲሁም በባንኩ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 20 እና 21 መሠረት ቅዳሜ ታህሳስ 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የአድዋ ድል መታሰቢያ የፓን አፍሪካ አደራሽ ስለሚካሄድ የተከበራችሁ የባንኩ ባለአክስዮኖች በዕለቱ በጉባኤዎቹ ላይ እንድትገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

1. ስለ አክሲዮን ማህበሩ መግለጫ

1.1. የአክሲዮን ማህበሩ ስም፡- ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ.

1.2. የዋና መስሪያ ቤት አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ ፣ ወረዳ 07

1.3. የንግድ ምዝገባ ቁጥር፡- KK/AA/3/0005948/2006

1.4. የሥራ ፍቃድ ቁጥር፡- LBB/018/2012

1.5. የተፈረመ ካፒታል፡- ብር 5,000,000,000.00

1.6. የተከፈለ ካፒታል፡- ብር 5,000,000,000.00

1.7. የባንኩ ድረ ገጽ፡- https://www.globalbankethiopia.com/

2. የ13 ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

2.1. የጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ፣

2.2. እ.ኤ.አ. በ2024/25 የሂሳብ ዓመት የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችንና አዳዲስ አክሲዮኖችን ሽያጭ ማሳወቅ፣

2.3. እ.ኤ.አ. የ2024/25 ሂሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድን ሪፖርት ማድመጥ፣

2.4. እ.ኤ.አ. የ2024/25 ሂሳብ ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማድመጥ፣

2.5. በተራ ቁጥር 2.3 ላይ በቀረበው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣

2.6. በተራ ቁጥር 2.4 ላይ በቀረበው የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣

2.7. እ.ኤ.አ. በ2024/25 የሂሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ ክፍፍል በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

2.8. እ.ኤ.አ. ከ2025/26 እስከ 2027/28 የሂሳብ ዓመታት የውጭ ኦዲተር መሾምና የአገልግሎት ክፍያውን መወሰን እና

2.9. እ.ኤ.አ. የ2024/25 ሂሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ዓመታዊ የስራ ዋጋ እና እ.ኤ.አ. የ2025/26 ሂሳብ ዓመት ወርሃዊ የአበል ክፍያ መወሰን ናቸው።

3. የ5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

3.1. የጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ፣

3.2. የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ በዳይሬክተሮች ቦርድ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን እና

3.3. የባንኩን መመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻል ናቸው።

4. ማሳሰቢያ

4.1. በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክስዮኖች ይህ የጥሪ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ ታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ከኢትዮጵያ ሆቴል በስተጀርባ ናሽናል ታወር ከሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 9ኛ ፎቅ ፋይናንስና አካውንትስ መምሪያ አክሲዮን (ሼር) ክፍል በመገኘት የዉክልና ቅጽ በመሙላት ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን ካለው አካል በጉባኤው ላይ ለመገኘት እና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የተሰጠ የውክልና ማስረጃ ዋናውንና አንድ ቅጅ ይዞ በመምጣት በጉባኤው ላይ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እየገልጽን የባንኩ የአክሲዮን ባለቤቶች ራሳቸው መጥተው በጉባኤው ላይ እንዲሳተፉ እናበረታታለን።

4.2. የባንኩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚያሳይ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ)፤ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ይዛችሁ እንዲትቀርቡ፣ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የባንኩ ባለአክሲዮኖች ይህንኑ የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው እናሳውቃለን፡፡

4.3. በተጨማሪም የድርጅት ተወካዮች፤ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ወይም ተመሳሳይ የኃላፊነት ደረጃ ላይ ያሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም ድርጅቱን ወክለው እንዲገኙ የሚያረጋግጥ የተመዘገበ ቃለጉባኤ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን ካለው አካል የተሰጠ የውክልና ሰነድ ይዘዉ መቅረብ ያለባቸው መሆኑን እንገልጻለን፡፡

4.4. በስራ ላይ ያሉ የባንኩ የቦርድ አባላት እና ሠራተኞች በየትኛውም የባለአክሲዮኖች ጉባኤ ላይ ማንኛውንም ባለአክሲዮን ወክለው መሳተፍ አይችሉም።

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ዳይሬክተሮች ቦርድ

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

Djibouti positions itself as Horn of Africa logistics gateway with new WFP base handover

The Government of Djibouti has officially assumed full management...

Dangote Refinery launches historic $1.6B IPO

The Nigerian Exchange (NGX) officially launched the initial public...

IOM warns Sudan humanitarian system faces collapse within weeks without new funding

The International Organization for Migration (IOM) has issued an...

Safaricom surpasses 15 million subscribers as it marks five years

Safaricom is marking five years since it received a...

Africa’s economic momentum is building as savings and cross-border trade activity accelerate

Rising savings, increasing cross-border payment activity and growing participation...

Experts urge sovereign AI models tailored to African realities

Researchers and leaders across Africa have been urged to...

Addis Ababa deploys digital monitoring Apps to track urban air quality

The Addis Ababa Transport Bureau has announced the deployment...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img