Tuesday, March 10, 2026

ገቢዎች ሚኒስቴር ከ50 ሺህ ብር በላይ ግብይት ላይ የተሰጠውን የቫት ማቀናነስ ማብራሪያ ‘ለጊዜው ተፈጻሚ አይደረግ’ አለ

ገቢዎች ሚኒስቴር ከ50 ሺህ ብር በላይ በሆነ ጥሬ ገንዘብ የሚፈጸሙ የንግድ ግብይቶችን በተመለከተ የገንዘብ ሚኒስቴር ከሰሞኑ የሰጠውን ማብራሪያ በከፊል አግደ። በተለይም የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ማቀናነስ/ተመላሽ ጉዳይ ላይ የተሰጠው ማብራሪያ “ለጊዜው ተፈጻሚ እንዳይደረግ” የሚል መመሪያ አስተላልፏል።

የገንዘብ ሚኒስቴር በጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም. ማብራሪያው፣ በገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 የተቀመጠው ከ50 ሺህ ብር በላይ የጥሬ ገንዘብ ግብይት ገደብ ተፈፃሚ የሚሆነው ለገቢ ግብር ብቻ መሆኑንና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የግብዓት ታክስ የማቀናነስ መብትን እንደማይገድብ በዝርዝር አስቀምጦ ነበር።

በተጨማሪም፣ ገዥዎች ከገደቡ በላይ በጥሬ ገንዘብ ከከፈሉ፣ ትርፍ ግብር በሚሰላበት ጊዜ ትርፍ ክፍያው እንደተቀናሽ ወጪ እንደማይያዝ እንዲሁም ሻጮችም ከገደቡ በላይ ጥሬ ገንዘብ ከተቀበሉ እኩል የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል።ሆኖም የገቢዎች ሚኒስቴር በጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ባስተላለፈው የሰርኩላር ደብዳቤ ፤ የገንዘብ ሚኒስቴር የሰጠው የቫት ማቀናነስ ማብራሪያ አዋጁ የተፈለገበትን “የታክስ ስወራ ድርጊት ለማስቀረት” የሚለውን ዓላማ “በአግባቡ ያልተመለከተ” በመሆኑ ውይይት እንዲደረግበት በመግለፅ  ” የቫት ማቀናነስ/ተመላሽ ጉዳይ ለጊዜው ተፈጻሚ እንዳይደረግ አዟል።

በገቢ ግብር አዋጁ ላይ የተቀመጡት ሌሎች የጥሬ ገንዘብ ገደቦች፣ በተለይም ገዥዎች የተቀናሽ ወጪ መብታቸውን የሚያጡበት እና ሻጮች ቅጣት የሚጣልባቸው ድንጋጌዎች፣ ተግባራዊ እንደሚሆኑ ሚኒስትሩ አስታውቋል።በተጨማሪም፣ የገቢዎች ሚኒስቴር ገቢ ወይም ሽያጭ የለንም በማለት ባዶ የሚያሳውቁ ታክስ ከፋዮችን አነስተኛ አማራጭ ግብር ለማስከፈል የሚያስችል ዝርዝር ማብራሪያ ከገንዘብ ሚኒስቴር እስኪመጣ ድረስ፣ ቀደም ሲል በተሰጠው አሰራር እንዲስተናገዱ ማዘዙን ለካፒታል የደረሰው የአፈፃፀም መመሪያው ያመለክታል።

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

Somali  Regional  Education   Bureau  Invitation   for National  Competitive   Bid

Somali  Regional Education  Bureau invites  interested eligible  bidders  invites...

Sandford International School

Admission of National Students for Nursery, Reception, and Year...

Call for Audit Proposal

RTI International is an independent, nonprofit research institute dedicated...

Invitation for BID

RTI is an independent organization dedicated to conducting innovative,...

Invitation for BID

RTI is an independent organization dedicated to conducting innovative,...

National Alcohol

Company Name                                                         NATIONAL ALCOHOL & LIQUOR FACTORY...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img