Wednesday, June 24, 2026

የዶላር የመሸጫ ዋጋ በ1.2 በመቶ ቅናሽ አሳየ፤ ብሔራዊ ባንክ ያቀረበው 500 ሚሊዮን ዶላር ሙሉ በሙሉ ገዢ አላገኘም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፣ የአንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ የመሸጫ ዋጋ ካለፈው ሳምንት የ1.21 በመቶ ቅናሽ በማሳየት 153.25 ብር መውረዱን አስታውቋል።

ባንኩ ለዚህ ልዩ ጨረታ እጅግ ከፍተኛ የሆነ 500 ሚሊዮን ዶላር ለገበያ ያቀረበ ቢሆንም፣ የንግድ ባንኮች የጠየቁት መጠን ግን ካቀረበው በታች ሆኖ ተመዝግቧል።

ይህም ባለፉት ሳምንታት በገበያው ላይ ይታይ የነበረውን ከፍተኛ የምንዛሬ ፍላጎትና የዋጋ ጭማሪ የገታ ክስተት ሆኗል።

በዛሬው ልዩ ጨረታ ላይ በአጠቃላይ 30 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን፣ የቀረበው የፍላጎት መጠን 455.29 ሚሊዮን ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል።

ይህም ብሔራዊ ባንክ ካቀረበው 500 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 91.1 በመቶው ብቻ ገዢ ማግኘቱን የሚያሳይ ሲሆን፣ ቀሪው 44.71 ሚሊዮን ዶላር ወይም 8.9 በመቶው ሳይሸጥ መቅረቱን ካፒታል ጋዜጣ ለመረዳት ችሏል።

በጨረታው የተሳተፉት ሁሉም 30 ባንኮች የጠየቁትን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማግኘት የቻሉ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ማክሰኞ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጨረታ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ልዩነት አለው።

በወቅቱ ከቀረቡት 31 ባንኮች መካከል 21ዱ ወይም 67.7 በመቶው ብቻ ነበሩ አሸናፊ መሆን የቻሉት።

የዛሬው የጨረታ ውጤት ካለፈው ሳምንት መደበኛ ጨረታ ጋር ሲነፃፀር በዋጋ ረገድም መጠነኛ መረጋጋት የታየበት ነው።

ባለፈው ማክሰኞ በተካሄደው 18ኛው ዙር ጨረታ ከፍተኛው የመግዣ ዋጋ 155.1299 ብር የነበረ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት ግን ወደ 154.00 ብር ዝቅ ብሏል። ይህም የ0.73 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።

በተመሳሳይ ዝቅተኛው የመቁረጫ ዋጋ ካለፈው ሳምንት 155.1010 ብር ወደ 152.0079 ብር ዝቅ ብሏል።

ይህም የምንዛሬ ገበያው ካለፈው ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲያሳይ የነበረውን ቀጣይነት ያለው የዋጋ ጭማሪ የሰበረ ሆኗል።

ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ያካሄደው ይህ ልዩ ጨረታ ለገበያው ያቀረበው የገንዘብ መጠን ከቀዳሚው ሳምንት የ70 ሚሊዮን ዶላር አቅርቦት ጋር ሲነፃፀር በ614 በመቶ ብልጫ አለው።

ይህ ከፍተኛ የዶላር አቅርቦት በገበያው ውስጥ ያለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍና የጥቁር ገበያውን ጫና ለመቀነስ ያለመ መሆኑ ይታወቃል።

ባንኩ በቀጣይም በወጣው መርሃ-ግብር መሠረት መሰል የውጭ ምንዛሬ ጨረታዎችን ማካሄዱን እንደሚቀጥል በመግለጫው አረጋግጧል።

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

Guterres Slams Fossil Fuel Windfall Profits, Urges Nations to Tax Extra Gains

The Secretary-General of the United Nations, António Guterres, has...

How Construction Professionals Are Using Short-Form Video to Land High-Paying Engineering Roles

The job market for engineers has been drastically revolutionized....

Exclusion from Investment Code Identified as Main Obstacle to Ethiopia’s Creative Industry

Stakeholders say the main obstacle facing Ethiopia’s cultural and...

“Resilience and Inclusion” Art Exhibition opens for World Refugee Day

An art exhibition themed “Resilience and Inclusion” opened today...

REQUEST FOR PROPOSALS FOR

REHABILITATION/RECONSTRUCTION OF WASH FACILITIES FOR 8 SCHOOLS IN THE...

Tender Notice

Date: 19 June 2026 The Office of the United Nations...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img