Friday, October 2, 2026

የ2019 አዲስ ዓመት ገበያ ቅኝት፡ ከፍተኛ ጭማሪ ታይቶበታል

በዕንቁጣጣሽ በዓል ዋዜማ የአዲስ አበባ ገበያዎች ከወትሮው የተለየ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እና የግብይት ውጥረት አስተናግደዋል። በከተማዋ በሚገኙ እንደ ፣ አቂቃ፣ ኮልፌ እና ካራ (ኮተቤ) የመሳሰሉ ታዋቂ የቁም እንስሳት ማዕከላት፣ በዓሉን አስመልክቶ የቀረቡት የእንስሳት ዋጋ ከቀደምት በዓላት በተለየ መልኩ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።

እነዚህ ቦታዎች በተለይም በበዓላት ወቅት እጅግ በጣም በርካታ የእርድ እንስሳት የሚቀርቡባቸው ዋና ዋና ማዕከላት እንደመሆናቸው መጠን፣ የዘንድሮው የገበያ ሁኔታ ከባድ የኑሮ ውድነት የታየበት ሆኗል።

በነዚህ ታዋቂ የገበያ ማዕከላት ካፒታል ባደረገው ምልከታ የቀንድ ከብቶች ዋጋ ከፍተኛ አኃዝ ይዞ መገኘቱን ለመታዘብ ተችሏል። ትልቅ የሚባሉት የእርድ ከብቶች እስከ 200,000 ብር ሲሸጡ፣ ዝቅተኛዎቹ ደግሞ በአማካይ ከ90,000 ብር ጀምሮ ተጠቃሚውን እየተፈታተኑ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል የአዲስ ዓመት የዶሮ ገበያ ከፋሲካ በዓል ጋር ሲነፃፀር ጨምሯል። መጠናቸው እንደ ሁኔታው የሚለያይ ሲሆን፤ ዝቅተኛው የዶሮ ዋጋ 1,400 ብር ሲሆን ከፍተኛው እስከ 3,500 ብር እየተጠራ ነው። ይህም ፋሲካ በዓል ላይ ከነበረው 1,300 ብር አማካይ ዋጋ ጋር ሲታይ የዕድገት ምጣኔውን ያሳያል። ከዕለት ተዕለት ፍጆታዎች ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዘው የዕቁላል ዋጋም አሻቅቦ የሀበሻ (የአገር ውስጥ) ዕቁላል 32 ብር፣ የፈሪንጁ (የውጭ/የድብልቅ) ደግሞ እስከ 28 ብር እየተሸጠ ነው።

​ሸማቾች ለካፒታል እንዳሉት የዋጋው ጭማሪ በእዚህ ልክ ይሆናል ተብሎ ያልተጠበቀ እና ኪሳቸውን የፈተነ መሆን አስረድተዋል። በዓሉን በቻሉት አቅም ለማሳለፍ ሲጥሩ፣ የዶሮ እና የሌሎች የፍጆታ ዕቃዎች መወደራቸው ከገቢያቸው ጋር የማይጣጣም በመሆኑ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ጥሏቸዋል። በሌላ በኩል የቁም እንስሳት ነጋዴዎች ዋጋው እንዲጨምር የተደረገው በራሳቸው ፍላጎት እንዳልሆነ ይገልራሉ። አሁን ፈታኝ ከሆነው የመኖ ዋጋ እና ከሌሎች ወጪዎች አንፃር ምንም ማድረግ ስለማንችል ነው ጭማሪውን ያደረግነው ሲሉ የንግዱን እውነታ ያብራራሉ።

​የኢትዮጵያ ስታቲክስ አገልግሎት ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያሳየው፣ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 15.1 በመቶ ደርሷል። የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ 14.9 በመቶ የጨመሩ ሲሆን፤ በዋናነት አትክልት 12.1 በመቶ፣ ስጋ 22.6 በመቶ፣ የወተት ተዋፅኦዎች እና እንቁላል 18.7 በመቶ፣ ፍራፍሬ 19.1 በመቶ፣ ዘይት እና ቅቤ 18.8 በመቶ፣ እንዲሁም ስኳር እና የምግብ ምርቶች 16.8 በመቶ ጭማሪ አሳይተዋል።

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

Unlock the Best Pusoy Free Game Experience on GameZone

Some card games rely almost entirely on luck. Pusoy...

Eritrea severely cuts all diplomatic ties with Ethiopia following Embassy closure and expulsion of staff

Diplomatic relations between Eritrea and Ethiopia have completely broken...

Addis Ababa Scenery Enters Final Development Stages

London-based developer iniBuilds has announced that its highly anticipated...

Ethiopia officially closes embassy in Eritrea, expels diplomats

The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia announced the...

EIH unveils $55 million Hilton Garden Inn development

The Ethiopian Investment Holdings (EIH) has unveiled a major...

Ethiopian Airlines Signs Boeing Deal for New 10 Freighters

Ethiopian Airlines has signed an agreement with Boeing to...

If Ethiopia’s Economy Is Growing, How Are Its Workers Living?

I recently listened to an episode of the International...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img