Tuesday, November 25, 2025

ኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰተ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ሳቢያ የሕንድ በረራዎች ተሰረዙ

በኢያሱ ዘካሪያስ

በአፋር ክልል ኤርታሌ አቅራቢያ በ10 ሺህ ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከሰተ በተባለ ፍንዳታ ምክንያት የህንድ አየር መንገዶች በረራዎችን መሰረዛቸው ተገልጿል።

​በሰሜን-ምስራቅ ኢትዮጵያ አፋር ክልል ኤርታሌ እሳተ ገሞራ አቅራቢያ የሚገኘው የሐይሊ ጉቢ እሳተ ገሞራ ከትላንት በስቲያ እሁድ (ኅዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም.) ከሺህ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ፍንዳታ ማድረጉን ተከትሎ ዓለም አቀፍ የአየር ትራፊክ ከፍተኛ መስተጓጎል ገጥሞታል።

ከፍንዳታው የወጣው አመዳማ ደመና በርካታ አገራትን ተሻግሮ የህንድ ሰማይን በመሸፈኑ የህንድ አየር መንገዶች የሆኑት ኤር ኢንዲያ እና አካሳ ኤር በረራዎችን ለመሰረዝ ተገደዋል።

​የህንድ አየር መንገዶች ማክሰኞ ዕለት ባወጡት መግለጫ፣ ከፍንዳታው የወጣው አመድ የአየር መንገዱን እንቅስቃሴ በማወኩ የተወሰኑ በረራዎችን መሰረዛቸውን አስታውቀዋል።

​ኤር ኢንዲያ የህንድ አቪዬሽን ተቆጣጣሪዎች ባወጡት መመሪያ መሠረት፣ በፍንዳታው አካባቢዎች ላይ በረሩ አውሮፕላኖች ላይ የጥንቃቄ ፍተሻ ለማድረግ በማሰብ ከሰኞ እስከ ማክሰኞ ባሉት ሁለት ቀናት 11 በረራዎችን ሰርዟል።

​ትንሹ አየር መንገድ አካሳ ኤር ደግሞ በተመሳሳይ ቀናት ወደ መካከለኛው ምስራቅ መዳረሻዎች ማለትም ወደ ጄዳህ ፣ ኩዌት እና አቡ ዳቢ የሚደረጉ በረራዎችን መሰረዙን ሮይተርስ ዘግቧል።

​የህንድ ሲቪል አቪዬሽን ሚኒስቴር እንዳለው፣ ጥቂት በረራዎች ብቻ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ መንገዳቸው የተቀየረ ሲሆን፣ የአየር ማረፊያዎች ባለስልጣን ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አውሮፕላኖች ሁሉ ማሳሰቢያ መስጠቱን ገልጿል።

​የአፋር ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ፍንዳታው “ከወትሮ በተለየ መልኩ የመጠን እና የድምፅ አስደንጋጭነት” እንደነበረው ገልጿል። የድምፁ ስሜት እስከ ጅቡቲ፣ ትግራይ እና ወሎ ዙሪያ ባሉ ከተሞች ላይ እንደተሰማም ዘገባዎች ያመለክታሉ።

ዓለም አቀፍ የእሳተ ገሞራ ክትትል ኤጀንሲዎች እንደዘገቡት ከሆነ፣ ፍንዳታው በኪልበቲ ራሱ ዞን፣ አፍዴራ ወረዳ በ8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከፍተኛ የድምፅ አስደንጋጭነት እንደነበረውና ጭስና አመድ መሳይ ብናኝ ማስከተሉ ተገልጿል።

ይህ ክስተት በአካባቢው ከ10 ሺህ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ ሊሆን እንደሚችል ታምኖበታል።

እነዚሁ የክትትል ኤጄንሲዎች እንደዘገብት የፍንዳታው ጭስ እንቅስቃሴ ከመቀነሱ በፊት እስከ 13.7 ኪ.ሜ (45,000 ጫማ) ወደ ሰማይ ከፍ ማለቱን ገልጿል።

በተመሳሳይ መልኩ የሲምሶኒያ የዓለም አቀፍ የእሳተ-ገሞራ መርኃ ግብሩ ላይ የተመዘገቡ ሰነዶችን ጠቅሶ እንደዘገበው ደግሞ፦ የሐይሊ ጉቢ እሳተ ገሞራ ላለፉት 12,000 ዓመታት ተከስቶ አያውቅም።

​የፍንዳታው ኃይለኛ ድምፅ እስከ ጅቡቲ፣ ትግራይ እና ወሎ ዙሪያ ባሉ ከተሞች ላይ እንደተሰማ ነዋሪዎች መናገራቸውን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

​የህንድ ሚቲዎሮሎጂ ዲፓርትመንት (IMD) ባወጣው መግለጫ፣ ከኢትዮጵያ የወጣው አመድ የመንና ኦማንን አቋርጦ ማክሰኞ ዕለት የፓኪስታን እና የሰሜን ህንድ ክፍሎችን ሸፍኖ ነበር። በአሁኑ ጊዜ የአመዱ ደመና ወደ ቻይና አቅጣጫ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ ማክሰኞ ህዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ላይ የህንድ ሰማይን ለቆ እንደሚወጣ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል ፤ ይህ በአፋር ክልል ኤርታሌ አቅራቢያ በተከሰተው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ምክንያት የተፈጠረው ጭስ እና አመዳማ ብናኝ በጤና ላይ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል የአፋር ክልል ጤና ቢሮ በትላንትናው ዕለት አስጠንቅቋል።

የቢሮው ኃላፊ ያሲን ሃቢብ እንደገለጹት ፣ ብናኙ በተለይም በመተንፈሻ አካል ላይ የጤና ችግር ሊያስከትል ስለሚችል ህብረተሰቡ አፍና አፍንጫን በመሸፈኛ መሸፈን ይገባዋል።

በተለይም አስም፣ ብሮንካይትስ እና ተያያዥ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች ይበልጥ መጠንቀቅ እንዳለባቸው አስገንዝበው፣ ክልሉ አስቸኳይ ህክምና አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን አክለዋል።

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

Tender Notice

The Office of the United Nations High Commissioner for...

REQUEST FOR EXPRESSION OF INTEREST (EOI)

Title of the EOI: The Provision of Asphalt Roads and...

Vacancy Announcement

November 21, 2025 Nib Insurance Company (S.Co) invites competent and...

About Every ones World

EveryonesWorld is a small leadership development and human-systems organization....

ChildFund Empowering Youth for Climate Action

ChildFund Ethiopia is a non-governmental organization dedicated to the...

EU-africa summit to drive 250 billion euro investment

at the upcoming 7th african union and european union...

AI Journey 2025 brings together AI scientists worldwide for overall progress of humankind

By our staff reporter The three-day AI Journey conference has...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img
Previous article