Monday, March 2, 2026

አይኤምኤፍ ለኢትዮጵያ 261 ሚሊዮን ዶላር እንዲለቀቅ የባለሞያዎች ደረጃ ስምምነት ላይ ደረሰ

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ከኢትዮጵያ ጋር በ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ የብድር ፋሲሊቲ መርሃግብር በአራተኛው ግምገማ ላይ በባለሞያዎች ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሱን አስታውቋል።

ይህ ስምምነት የአይኤምኤፍ ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ሲያጸድቀው፣ ቀጣዩ የ261 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ለኢትዮጵያ እንዲለቀቅ መንገድ ይከፍታል። ይህ ክፍያ ሲፈጸም በአጠቃላይ በፕሮግራሙ ስር ለኢትዮጵያ የተሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ወደ 2.13 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ይላል።

የገንዘብ ተቋሙ ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የጀመረውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማረጋጋት እና የልማት ማሻሻያዎችን በመገምገም፣ “የተሃድሶውን ፍጥነት ማስቀጠል የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማጠናከር እና በመካከለኛ ጊዜ ዕድገትንና ድህነትን ለመቀነስ ቁልፍ ይሆናል” የሚል አስተያየት ሰጥቷል።

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በሐምሌ 2024 የድጋፍ ብድሩን ስትይዝ፣ ከባድ የውጭ ዕዳ መልሶ የማዋቀር ሥራ ላይ ትገኛለች። አይኤምኤፍ ባወጣው ሪፖርት፣ በG20 የጋራ ማዕቀፍ ስር የዕዳ ዘላቂነትን ለመመለስ የሚደረጉ ጥረቶች እየገፉ መሆናቸውን ጠቁሟል።

ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ከሁለትዮሽ አበዳሪዎች ጋር በመደበኛ ዕዳዋ ላይ ስምምነት ላይ ብትደርስም፣ ባለሀብቶች ከ1 ቢሊዮን ዶላር የዩሮቦንድ ጋር በተያያዘ በሚደረገው የዕዳ ቅናሽ መጠን ላይ አለመግባባት መኖሩ የሂደቱን መጓተት እንዳስከተለ ይታወቃል።

በአይኤምኤፍ የባለሞያዎች ቡድን መሪ በሆኑት በአልቫሮ ፒሪስ የሚመራው ቡድን ከጥቅምት 20 እስከ ህዳር 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ በአዲስ አበባ በመገኘት፣ በአይኤምኤፍ የተራዘመ የብድር ፋሲሊቲ መርሃግብር ስር በአራተኛው ግምገማ ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል። ይህ ተከትሎ ደግሞ ከህዳር 24 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የቀጠለው ዉይይት በአዲስ አበባ ተካሄዶ ነበር።

ሚስተር ፒሪስ እንደተናገሩት ፤ ​“የአይኤምኤፍ ባለሞያዎች ቡድን እና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በተራዘመ የብድር ፋሲሊቲ ስምምነት ስር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ፕሮግራም በአራተኛው ግምገማ ላይ በባለሞያዎች ደረጃ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ስምምነቱ በሚቀጥሉት ሳምንታት የአይኤምኤፍ ማኔጅመንት እና ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ማጽደቅ ይጠበቅበታል።

የማሻሻያውን ፍጥነት ማስቀጠል የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማጠናከር እና በመካከለኛ ጊዜ ዕድገትንና ድህነትን ለመቀነስ ቁልፍ ይሆናል ያሉት አልቫሮ የዋጋ ግሽበትን ለመግታት ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ መከተል ተገቢ እንደሆነ አፅንኦ ሰጥተዉ ተናግረዋል ።

የባለሞያዎች ቡድን ከአስተዳዳሪዎች ጋር ባለፈዉ ሳምንት በኢትዮጵያ በነበራቸዉ ቆይታ ከገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካለኝ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝቶ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

The Napkin Curve and the Limits of Economic Policy

Few images in modern economics are as simple—or as...

GERD: Africa’s energy Project of the Year

The Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) has reached a...

Yohannes Names Backroom Staff Following National Team Reappointment

Yohannes Sahle, who was recently reinstated as the head...

No More Midnight Transactions: Ethiopia Steps Into the Light

I remember sitting in my office in 2019 with...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img