Friday, January 23, 2026

አላይድ ጎልድ በመጪዉ ሚያዚያ ወር በኢትዮጵያ የወርቅ ምርት ሊጀምር መሆኑ ተገለጸ

የካናዳው “አላይድ ጎልድ” ኩባንያ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው የኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት በመጪው ሚያዝያ ወር ስራ እንደሚጀምር አስታወቀ። ኩባንያው ፕሮጀክቱ በ2026 ሶስተኛ ሩብ ዓመት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወደ ምርት እንደሚሸጋገር የገለጸ ሲሆን፣ በየዓመቱ 290 ሺህ አውንስ ወርቅ ለማምረት አቅዷል።

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ፒተር ማሮን እንደገለጹት፣ ኩባንያው ለፍለጋ ስራ በየዓመቱ 8 ሚሊዮን ዶላር የመደበ ሲሆን፣ በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ የወርቅ ክምችቱን ወደ 5 ሚሊዮን አውንስ ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል።

ማዕድን ማውጫው ከሰፈራ መንደሮች ርቆ የሚገኝ በመሆኑ ምንም ዓይነት የህዝብ ማፈናቀል ስራ እንዳልተከናወነ የጠቀሱት ስራ አስፈጻሚው፣ ድርጅታቸው የአካባቢውን ነዋሪዎች በቅድሚያ ለመቅጠር ፖሊሲ ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ኩባንያው በኢትዮጵያ ምርት ሊጀምር መሆኑን ተከትሎ የአክሲዮን ዋጋው ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በአራት እጥፍ በማደግ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል።

አላይድ ጎልድ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በማሊ እና በኮትዲቯር ግዙፍ የወርቅ ማዕድን ማውጫዎች እንዳሉት ይታወቃል።

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

በአልኮል እና በትምባሆ ላይ የሚጣለው ‘የጤና ተኮር ታክስ’ ለሕክምና አገልግሎት ድጎማ ሊውል ነው

የኢትዮጵያ መንግሥት በጤናው ዘርፍ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ለማሳደግ እና...

ደቡብ ሱዳን በ2026 የአፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እንደምታስመዘግብ ተተነበየ

የአፍሪካ ደሀና በጦርነት ክፉኛ የተጎዳችው ደቡብ ሱዳን፣ እ.ኤ.አ በ2026...

አዋሽ ካፒታል እና ገዳ ሴኩሪቲስ የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ የንግድ አባላት ሆኑ

የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ አዋሽ ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ...

በኢትዮጵያና በአምስት የአፍሪካ ሀገራት የፀሐይ ኃይል ግብርናን ለማስፋፋት የ50 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ተፈቀደ

የአለም ባንክ እና የሮክፌለር ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ጨምሮ በስድስት የአፍሪካ...

አይ.ኤፍ.ሲ በኢትዮጵያ ለሚከናወኑ የሸራተን ሆቴል ፕሮጀክቶች የ80 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለመስጠት እቅድ መያዙ ተነገረ

የዓለም ባንክ የግል ዘርፍ አበዳሪ የሆነው ኢንተርናሽናል ፋይናንስ ኮርፖሬሽን...

Concurrently Maintainable: Why Tier III Data Centres Are the Real Play for East Africa

By Demos Kyriacou East Africa's digital economy is expanding at...

Why ending child marriage is key for seizing Africa’s demographic dividend

Africa’s future prosperity needs its girls… Africa is home to...

The Prosperity Gospel And The Mirage Of Real Development

Across much of the Global South, and increasingly beyond...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img