የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በ2018 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከብር 11.3 ቢሊዮን በላይ ጠቅላላ የአርቦን ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል።
ይህ ውጤት ድርጅቱ ከታለመው ግብ በ8.5% እንዲበልጥ ያስቻለው ሲሆን፣ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር አስደናቂ የሆነ የ58% ዕድገት ማሳየቱን ጠቁሟል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ ድርጅቱ የኢንቨስትመንት ገቢ ብር 316 ሚሊዮን በመድረስ የ102.5% ዕድገት ማስመዝገቡን የገለፀ ሲሆን አስተማማኝ የመድን መፍትሄዎችን በማቅረብ እና በኢንዱስትሪው ውስጥ ዘላቂ ዕድገትን በማስመዝገብ ረገድ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።


