Thursday, March 26, 2026

ሁሉም ባንኮች አዲስ እና ነባር ሂሳቦችን ለማስተሳሰር ወደ VeriFayda 2 እንዲሸጋገሩ ተወሰነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ከሁሉም ባንኮች የደንበኞች ሂሳብ ቁጥር ጋር የማጣመር ስራ በይፋ መጀመሩን አስታውቀዋል።

ይህ ውህደት የፋይናንስ ዘርፉን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስኬድ ወሳኝ ምዕራፍ እንደሆነ ተመላክቷል።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከሁሉም ባንኮች የደንበኞች ባንክ ሂሳብ ቁጥር ጋር የማጣመር (Harmonization) ስራ በይፋ መጀመሩን ተከትሎ፣ ባንኮች ቀደም ሲል ይጠቀሙበት የነበረውን VeriFayda 1 (old eKYC) ስርዓት ሙሉ በሙሉ ትተው ወደ ይበልጥ ዘመናዊ እና የተቀናጀው VeriFayda 2 እንዲሸጋገሩ ተወስኗል።

​VeriFayda 2 በኢቲስዊች (EthSwitch) በኩል የሚቀርብ ሲሆን፣ ባንኮች አዲስ ሂሳብ ለመክፈት (New Account Opening) እንዲሁም ነባር ሂሳቦችን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር (Existing Account Harmonization) ይህንኑ አዲስ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

ይህ የመረጃ ስርዓት ባንኮች የደንበኞቻቸውን ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ ከማስቻሉም በላይ፣ በሀሰተኛ ማንነት የሚከስት የገንዘብ መጭበርበርን ለመከላከል እንደ ቁልፍ የዲጂታል መሰረተ ልማት ያገለግላል።

ለባንኮች ወደ VeriFayda 2 የማሸጋገሪያ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶ ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም. መሰራጨቱ ተመላክቷል።

የፕሮግራሙ እና የኢቲስዊች የቴክኖሎጂ ባለሞያዎች ባንኮች የማሸጋገር ሥራውን በተሳካ ሁኔታ እንዲያከናውኑ የቴክኒክ ድጋፍ እና ክትትል እያደረጉ ሲሆን፣ በቀጣይም ድጋፉ የሚቀጥል ይሆናል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የባንክ ደንበኞች እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ መረጃ ጋር እንዲያጣምሩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ይህንን ለማድረግ ደንበኞች ወደ ባንክ ቅርንጫፎቻቸው በአካል በመሄድ ወይም ባንኩ በሚያስቀምጠው አሰራር መሰረት ኦንላይን የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥራቸውን (06 አUዝ-FAN Number) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

ሁለቱ ተቋማት እንዳስታወቁት ፤ ለፋይዳ ያልተመዘገቡ ደንበኞች ደግሞ በቅድሚያ በአቅራቢያቸው በሚያገኙት የፋይዳ ምዝገባ ጣቢያ መመዝገብ እንዳለባቸው ተገልጿል።

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

From Check-Out to Check-In: The Ethiopian Hotel Industry’s Reinvention

In the global imagination, hotels are symbols of movement,...

“I Walked Into Fire”: Inside the Emotional Journey Behind the ET302 Memorial

Seven years after the Ethiopian Airlines Flight 302 crash,...

The Quiet Cost of a War Far Away

Wars have a way of traveling. They begin with missiles...

France honors Ethiopian music legend Girma Beyene with Prestigious Arts and Letters Title

Renowned Ethiopian composer, pianist, and arranger Girma Beyene has...

Ethiopia’s drive toward fiscal discipline: Pragmatic or idealistic?

The Ethiopian government has embarked on fiscal consolidation effectively...

Name: Amare Tesfaye

2. Education: (የት/ት ደረጃ)     10+ 3. Company name: (የመስሪያ ቤቱ ስም)     Ak...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img