Thursday, November 13, 2025

የውጭ ትምህርት ቤቶች 30% ከሀገራቸው መንግሥት ድጋፍ ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ የሚያስገድድ ረቂቅ ደንብ ይፋ አደረገ

​ትምህርት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት የሚመሩበትን አዲስ ረቂቅ ደንብ ማዘጋጀቱን ያስታወቀ ሲሆን፣ ረቂቁ በተለይ በውጭ ሀገር ማኅበረሰቦች ለሚቋቋሙ ትምህርት ቤቶች አስገዳጅ መስፈርቶችን አኑሯል።

ካፒታል የተመለከተዉ ​ረቂቅ ደንቡ እንደሚያስገድደው፣ በውጭ ሀገር ማኅበረሰብ የተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች ከጠቅላላ በጀታቸው ውስጥ 30% (ሰላሳ በመቶ) የሚሆነው ከሀገራቸው መንግሥት ድጋፍ ማግኘታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ቀሪውን 70% ደግሞ ራሳቸው መሸፈን የሚችሉ መሆናቸውን የሚያሳይ ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ ግዴታ ተጥሏል።

​ይህ የፋይናንስ ማረጋገጫ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና አግባብ ባለው የሰነዶች ማረጋገጫ ባለሥልጣን ተረጋግጦ መቅረብ እንዳለበት ደንቡ ያመለክታል። ሚኒስቴሩ ይህን መስፈርት ያኖረው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የፋይናንስ መረጋጋትና አስተማማኝነት ለማረጋገጥ ያለመ እንደሆነ ይጠበቃል።

በዚህ ለትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት አስተያየት ክፍት በተደረገዉ አዱሱ ረቂቅ ደንብ፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት የአገሪቱን የትምህርት ሕግ፣ የመምህራን ብቃት፣ የተማሪዎች መብት እና የትምህርት ደረጃን ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ ሕጎችን ማክበር ይጠበቅባቸዋል።

በዚህ ደንብ ላይ እንደተገለፀዉ ፤​ተቋማቱ የራሳቸው የሆነ የገንዘብ ምንጭ (ከተማሪዎች ክፍያ፣ ከስጦታ ወይም ከኢንቨስትመንት ትርፍ) እና ነጻ አስተዳደር ያለው ድርጅታዊ አወቃቀር ሊኖራቸው ይገባል።

​ረቂቅ ደንብ ላይ ሚኒስቴሩ ተቋማት ሊያስከፍሉት የሚችሉትን የትምህርትና ሌሎች አገልግሎት ክፍያዎችን ጣሪያ በተመለከተ መመሪያ እንደሚያወጣና በየሦስት ዓመቱ እንደሚስተካከል ደንግጓል። የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ ከ3 ወራት በፊት ተጠቃሚዎችን ማወያየት እንደሚኖርባቸው ያስገድዳል።

​መንግሥታዊ ያልሆኑ የአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴሩ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንደገና መመዝገብ እንዳለባቸው የተገለፀ ሲሆን ተቋማት የልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ምቹ ሁኔታን መፍጠር እና ተማሪዎቻቸው ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ የትምህርት የምክር አገልግሎት ማግኘታቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው አስታዉቋል።

ትምህርት ሚኒስትሩ ​አዲሱ ደንብ የመንግሥታዊ ያልሆኑ ትምህርት ተቋማትን ምዝገባ፣ ዕውቅና እና ቁጥጥር በአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1368/2017 መሠረት የሚያከናውን መሆኑን በግልጽ አስረድቷል።

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

የአፍሪካ ኅብረት ዕዳን ለመቋቋም “አዲስ የፋይናንስ ስምምነት” እና ፍትሐዊ የክፍያ ሁኔታዎችን ጠየቀ

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፤ አህጉሪቱ ከዓለም...

ፍርድ ቤቱ በኢትዮጵያና በአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤቶች ሕንፃ ውዝግብ ላይ የእግድ ውሳኔ አስተላለፈ

በኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት (ኢትዮጵያ ቻምበር) እና...

Re: CALL FOR EXTERNAL AUDIT SERVICES

Initiative Africa (IA), an Ethiopian Resident Charity dedicated to...

Invitation To Tender

For the supply of Vegetable seed Tender Reference -...

የባለአክስዮኖች 13ኛ መደበኛ እና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤዎች የስብሰባ ጥሪ

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. የባለአክስዮኖች 13ኛ መደበኛ እና 5ኛ...

Invitation to international competitive Bid (ICB)

Procurement of 10 units Electric Express Buses (61 seat)...

PROVISION OF VARIOUS OUTSOURCED SERVICES

FOR WFP OFFICES LOCATED IN THE COUNTRY Ref: EOI-003-2025 The United...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img