Thursday, September 17, 2026

በጥቁር ገበያ ያለው የምንዛሬ ዋጋ ልዩነት ወደ 13 በመቶ ከፍ ማለቱ ተነገረ

በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ካለው አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ማዕቀፍ ውስጥ ዋነኛው የሆነው የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲወሰን የማድረግ ሂደት፣ አሁንም በተለያዩ መዋቅራዊ ችግሮች ሳቢያ ተግዳሮት እየገጠመው መሆኑ ተጠቆመ።

በተለይም በባንኮች እና በትይዩ ገበያ (ጥቁር ገበያ) መካከል ያለው የዋጋ ልዩነት በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ወደ 13 በመቶ ከፍ ማለቱ ተመልክቷል።

የአለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እንዳስታወቀው፤ ከመስከረም እስከ ጥቅምት አጋማሽ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በይፋዊው የባንክ ተመን እና በጥቁር ገበያው መካከል ያለው ልዩነት ከ10 በመቶ በታች ወርዶ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ልዩነቱ በድጋሚ እያገረሸ መምጣቱን አመልክቷል።

ለዚህም እንደ ዋና ምክንያት የተቀመጠው፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ምንዛሬን ከጨረታ ውጭ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሸጡ ነዉ ያለዉ ድርጅቱ ይህም የምንዛሬ ተመኑ በገበያ ውስጥ ያለውን ትክክለኛ የፍላጎት እና የአቅርቦት ሁኔታ እንዳያንጸባርቅ አድርጎታል።

በተጨማሪም ብሔራዊ ባንክ በሚያካሂደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ላይ ባንኮች ሊያገኙ የሚችሉት ድርሻ ላይ ገደብ መቀመጡ፣ ባንኮች ያላቸውን የምንዛሬ ፍላጎት በነፃነት እንዳያሟሉ እና ትክክለኛ የዋጋ ግኝት እንዳይኖር እንቅፋት ሆኗል።

ካፒታል ጋዜጣ ከ አይኤምኤፍ ሪፖርት ላይ እንደተመለከተው፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደ ሀገር ስትራቴጂካዊ የሆኑ የነዳጅ እና የማዳበሪያ ግዢዎችን በብቸኝነት እንዲሸፍን መደረጉ፣ በባንኩ ላይ ያለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት አሁንም በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀጥል አድርጎታል።

የግል ባንኮች እነዚህን ግዙፍ ሀገራዊ ሸክሞች ለመጋራት ያላቸው ፍላጎት አነስተኛ መሆኑ፣ በንግድ ባንክ ላይ ያለውን ጫና ከማክበዱም በላይ በገበያው ላይ የምንዛሬ እጥረት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል።

ምንም እንኳን በባንኮች መካከል የሚደረግ የምንዛሬ ግብይት የተጀመረ ቢሆንም፣ ሂደቱ አሁንም ቢሆን “እንደ አስፈላጊነቱ የሚከናወንና የተቀናጀ ባለመሆኑ፣ ባንኮች ያላቸውን ትርፍ የውጭ ምንዛሬ እርስ በርስ በብቃት እንዳያለዋውጡ አድርጓቸዋል።

የሀገሪቱ የወርቅ እና የቡና ኤክስፖርት ከፍተኛ እድገት እያሳየ ቢመጣም፣ በትይዩ ገበያ ላይ ያለው የዋጋ ልዩነት መስፋት በኢኮኖሚው ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል ነዉ የተባለዉ።

በኢያሱ ዘካሪያስ

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

Ethiopia’s National Emergency Medical Team Earns Historic WHO Classification

The World Health Organization (WHO) has successfully verified the...

Ethiopian Airlines dominates as Africa’s largest carrier with 2.1 million seats in September 2026

Total scheduled airline capacity across Africa reached 25.8 million...

Ethiopia, Kenya finalize preparations to scale up cross-border power trade by December 2026

Ethiopia is finalizing preparations to double its electricity supply...

Ethiopia records 824% remittance growth over the decade, accounting for 5% of national GDP

Ethiopia has rapidly ascended to become Africa’s fourth-largest remittance...

Ethiopia Rejects Commercial Buyback Offer for Looted 18th-Century Royal Gospel

The Ethiopian Heritage Authority has confirmed to Capital that...

Djibouti positions itself as Horn of Africa logistics gateway with new WFP base handover

The Government of Djibouti has officially assumed full management...

Dangote Refinery launches historic $1.6B IPO

The Nigerian Exchange (NGX) officially launched the initial public...

IOM warns Sudan humanitarian system faces collapse within weeks without new funding

The International Organization for Migration (IOM) has issued an...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img