Sunday, October 11, 2026

የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና የመላኪያ ፈቃድ አገልግሎት ከመጪው ሰኞ ጀምሮ በኦላይን ሊሆን ነዉ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለንግዱ ማኅበረሰብ የሚሰጠውን የሁለት ወሳኝ አገልግሎቶችን ማለትም የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባ እና የመላኪያ ፈቃድ አገልግሎት ከመጪዉ ሰኞ ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን (በበይነ መረብ) ሥርዓት ማዘመኑን አስታወቀ።

የንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አብዱልሀኪም ሙሉ እንዳስታወቁት፣ ይህ እርምጃ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለንግዱ ማኅበረሰብ የሚያቀርባቸውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በማዘመን ረገድ የወሰደው ሌላ ወሳኝ ምዕራፍ ነው።

ቀደም ሲል በማኑዋል ሲሰጥ የነበረው ይህ አገልግሎት ወደ ኦንላይን ሥርዓት ሙሉ በሙሉ መሸጋገሩ የአገልግሎቱን ተደራሽነት ከፍ ያደርጋል ተብሏል።

አብዱልሀኪም እንዳብራሩት፣ ይህ አዲስ የተዘረጋው ሥርዓት ላኪዎች የሚፈልጉትን አገልግሎት ከሰው ንክኪ ነጻ በሆነ መልኩ ባሉበት ቦታ ሆነው እንዲያገኙ ያስችላል። ይህም የተገልጋዮችን ጊዜና ወጪ ከመቆጠብም በላይ አገልግሎቱን ዘመናዊና ፍትሐዊ ያደርገዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም መንግስት የተገልጋዮችን እርካታ ለማረጋገጥ መጠነ ሰፊ ማሻሻያዎችን እያደረገ መሆኑን ገልጸው፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉና ወጪ ቆጣቢ እንዲሆኑ በትጋት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

ይህን ተከትሎ የንግድ ለመጀመር ይወስድ የነበረው ጊዜ ከ32 ቀናት ወደ 5 ቀን ወርዷል የተባለ ሲሆን ለንግድ ሥራ አጀማመር ይወስድ የነበረው ሂደት ደግሞ ከ11 ደረጃዎች ወደ 4 ደረጃዎች ዝቅ ማድረግ መቻሉን ካፒታል ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

FX volatility, capital pressures mount for enterprises following reforms

Import-dependent enterprises in Ethiopia are facing mounting working-capital pressures...

Engineers call for AI, BIM adoption to address skill gaps

Engineering leaders have called for the rapid adoption of...

A cabinet must deliver, not merely govern

Ethiopia’s newly formed federal government arrives at a moment...

Effective Altruism and the Global Economy: Can Wealth Do More Good?

The global economy has a strange contradiction at its...

Ethiopia showcases fashion heritage at BRICS+ Summit in Moscow

Ethiopia’s fashion industry was represented at the fourth BRICS+...

Engineers urge shift to local agricultural machinery manufacturing

Ethiopian agricultural engineers have called for greater investment in...

Agricultural bank set to begin operations within three months

Ethiopia’s planned Agricultural Bank is expected to begin operations...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img