Tuesday, October 13, 2026

በኢትዮጵያ ደቡባዊ እና ምስራቃዊ ክፍል ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ የዝናብ መክሸፍ አሳሳቢ የድርቅ አደጋ ደቀነ

በኢያሱ ዘካሪያስ

በኢትዮጵያ ደቡባዊና ምሥራቃዊ አካባቢዎች እንዲሁም በጎረቤት ሶማሊያና ኬንያ የተከሰተው የድርቅ አደጋ ወደ ከፋ ደረጃ ተሸጋግሯል። እ.ኤ.አ ከጥቅምት እስከ ታኅሣሥ 2025 ሊዘንብ ይገባ የነበረው ዝናብ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በመክሸፉ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ለከፋ የምግብ እጥረትና ለኑሮ መቃወስ ተጋልጠዋል።

በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ደቡባዊና ምሥራቃዊ ክፍሎች፣ እንዲሁም እንደ ቦረና እና ባሌ ያሉ አካባቢዎች ለሁለተኛ እና ለሦስተኛ ተከታታይ ወቅት የዝናብ እጥረት እያጋጠማቸው ይገኛል። እንደ ሪፖርቱ ገለጻ፣ በእነዚህ አካባቢዎች የጣለው የዝናብ መጠን ከመደበኛው በ70 በመቶ ያነሰ ሲሆን፣ ይህም ከ1973 ዓ.ም (1981) ወዲህ የታየ እጅግ ዝቅተኛው የዝናብ መጠን ሆኖ ተመዝግቧል።

ምንም እንኳን በመካከለኛውና በሰሜን የሀገሪቱ ክፍሎች የነበረው የ”መህር” አዝመራ መልካም የሚባል ቢሆንም፣ በደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች ያለው የ”ደይር/ሐጋያ” ዝናብ መክሸፍ በእንስሳት ሀብት ላይ የተመሰረተውን የነዋሪዎች ኑሮ ክፉኛ እየጎዳው ነው። በተለይም በምሥራቅ ሐረርጌ ቆላማ አካባቢዎች እጅግ አስከፊ የሆነ የምግብ ዋስትና እጥረት (IPC Phase 4) በ2026 መጀመሪያ ላይ ሊከሰት እንደሚችል ተተንብዮአል።

የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) መረጃ እንደሚያሳየው፣ በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ አዋሳኝ በሆነው “የማንዴራ ትሪያንግል” አካባቢ እስከ 95 በመቶ የሚሆነው የግጦሽ መሬት በድርቅ ተመቷል።

ከወትሮው የተለየ ከፍተኛ ሙቀት ከዝናብ እጥረቱ ጋር ተዳምሮ የአፈር እርጥበት እንዲጠፋና ዕፅዋት እንዲደርቁ በማድረጉ፣ የእንስሳት መኖና ውኃ ለማግኘት የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል።

ይህም የእንስሳት አካል እንዲከሳና ለሞት እንዲጋለጡ እያደረገ ሲሆን፣ ለሕፃናት ዋነኛ የአመጋገብ ምንጭ የሆነው የወተት ምርትም ሙሉ በሙሉ እንዲቆም አድርጓል። ይህም በክልሉ የሚገኙ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ሕፃናትን ለከፋ የአልሚ ምግብ እጥረት አጋልጧል።

ድርቁ ያስከተለው የውኃና የግጦሽ እጥረት መጠነ ሰፊ መፈናቀልን እያስከተለ ይገኛል። ከሶማሊያ ድርቅን ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ ጋሻሞ እና ቦክ ወረዳዎች የተሻገሩ ዜጎች ቁጥር ከ55,800 በላይ መድረሱ ተገልጿል። ይህ ፍልሰት ቀድሞውኑ ውስን በሆነው የኢትዮጵያ የአካባቢው መርጃ አቅም ላይ ተጨማሪ ጫና እየፈጠረ ይገኛል።

ከዚህም በተጨማሪ ሴቶችና ሕፃናት ውኃ ፍለጋ ረጅም ርቀት ለመጓዝ በመገደዳቸው ለጾታዊ ጥቃት የመጋለጥ እድላቸው መጨመሩንና በትምህርት ገበታቸው ላይም ከፍተኛ መስተጓጎል እየደረሰ መሆኑ ተጠቁሟል።

የረሃብና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት የሥራ ቡድን ከሰሞኑ ባወጣዉ አሳሳቢ ሪፖርት፣ የ2026 ዓ.ም ድርቅ ወደ ሰብዓዊ ጥፋት እንዳይቀየር ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል። እስካሁን ለሰብዓዊ እርዳታ የተገኘው የገንዘብ መጠን ከሚያስፈልገው ውስጥ 24 በመቶ ብቻ መሆኑ ስጋቱን የከፋ ያደርገዋል።

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

ERA advances pilot road safety star rating assessment with iRAP

The Ethiopian Roads Administration (ERA) is advancing a pilot...

KEFI resumes Tulu Kapi gold project development after fatal incident

KEFI Gold and Copper has resumed development activities at...

Djibouti’s ports face rising costs amid Red Sea shipping disruptions

Djibouti’s port sector is experiencing increased transshipment activity as...

KEGNA BEVERAGES

CALL FOR DISTRIBUTION OF PRODUCTS 1. Introduction More than 5,000 shareholders...

Invitation to Bid

Bid No. HB/002/2026 Hibret Bank has a Head Office Building...

BERHAN BANK S.C.

ብርሃን ባንክ አ.ማ Berhan Bank                         INVITATION FOR BIDS (IFB) BID EXTENSION NATIONAL...

Invitation to Bid for Audit Service

The Automotive Manufacturing Company of Ethiopia Share Company (A.M.C.E),...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img