Friday, January 30, 2026

አዲሱ የንብረት ታክስ አዋጅ ከታክስ ነጻ የሆኑ ተቋማት ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎት መዋጮ እንዲከፍሉ አዘዘ

በኢያሱ ዘካርያስ

የክልል መንግስታት ተግባራዊ እንዲያደርጉት የተዘጋጀው አዲሱ የንብረት ታክስ ሞዴል አዋጅ፣ በሕግ ከታክስ ነጻ የተደረጉ ንብረቶችና ተቋማት ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች ማካካሻ የሚሆን “በታክስ ምትክ የሚደረግ መዋጮ” እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ድንጋጌ ይፋ አደረገ።

ይህ ውሳኔ በከተሞች ውስጥ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በሁሉም ተጠቃሚዎች እንዲደገፉ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህ አዋጅ የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት ከቀጥተኛ የንብረት ታክስ ነጻ እንዲሆኑ ተደንግጓል። ሆኖም እነዚህ ተቋማት የሚገኙባቸው አካባቢዎች በከተማ አስተዳደሩ የሚከናወኑ እንደ መንገድ ጥገና፣ የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የጎዳና መብራት፣ የጽዳትና የደህንነት አገልግሎቶች ተጠቃሚ በመሆናቸው፣ ለእነዚህ አገልግሎቶች ማካካሻ የሚሆን መዋጮ እንዲከፍሉ ተደንግጓል።

እንደ ገንዘብ ሚኒስትር ማብራሪያ ከሆነ፤ የሃይማኖት ተቋማት ለአምልኮና ለመካነ መቃብር የሚጠቀሙባቸው ንብረቶች፣ ለህብረተሰቡ ነጻ ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ እንዲሁም የመንግሥት ቢሮዎችና ዲፕሎማቲክ ተቋማት የሚጠቀሙባቸው ንብረቶች ከታክስ ነጻ ቢሆኑም፣ እንደየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ “በታክስ ምትክ የሚደረግ መዋጮ” ሊጠየቁ ይችላሉ።

አዋጁ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ከታክስ ጫና ለመታደግ ግልጽ የሆኑ መስፈርቶችን ያስቀመጠ ሲሆን በዚህም፤ ዓመታዊ ገቢያቸው ከአገራዊ አማካይ የነፍስ ወከፍ ገቢ 50 በመቶ የማይበልጥ እና በማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የተረጋገጠላቸው “ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች” ከታክስ ነጻ ይሆናሉ።

በተጨማሪም ዋጋቸው በከተማ አስተዳደሮች ከአንድ ሚሊዮን ብር፣ በማዘጋጃ ቤት ከተሞች ከ250 ሺህ ብር፣ እንዲሁም በታዳጊ ከተሞች ከ100 ሺህ ብር ያነሰ የመኖሪያ ቤቶችና የቦታ ማሻሻያዎች ከንብረት ታክስ ነጻ ተደርገዋል።

በታክስ ምትክ የሚደረገው መዋጮ መጠንና ዓይነት በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በሚወጣ ደንብ የሚወሰን ሲሆን፣ አወሳሰኑም “ፍትሐዊ፣ ተገቢና ትርጉም ያለው” መሆን እንዳለበት ተደንግጓል።

በተጨማሪም የታክስ ነጻ መብት የተሰጣቸው አካላት በየዓመቱ የታክስ ዘመኑ ከመጠናቀቁ 60 ቀናት በፊት የዕድሳት ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ንብረቱ ለተሰጠው ዓላማ መዋሉን የሚያረጋግጡ ደጋፊ ሰነዶችን ማቅረብ የማይችሉ ወይም የባለቤትነትና የጥቅም ለውጥ አድርገው ሪፖርት ያላደረጉ አካላት፣ የታክስ ነጻ መብታቸው ሊሰረዝ ወይም ሊታገድ እንደሚችል አዋጁ ያስጠነቅቃል።

ይህ የተገለፀዉ የገንዘብ ሚኒስቴር ከሰሞኑ በሀገሪቱ የሚገኙ ከተሞች የራሳቸውን ገቢ በማሳደግ ጥራት ያለው መሠረተ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት እንዲያቀርቡ የሚያስችል “የሞዴል የንብረት ታክስ አዋጅ” አዘጋጅቶ ለክልል መንግስታት መላኩን ባሳወቀበት ደብዳቤ ላይ ነዉ።

ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ለክልሎች በላኩት ደብዳቤ ላይ እንደገለጹት፣ ይህ አዋጅ የከተማ አስተዳደሮች በየአካባቢያቸው የንብረት ታክስ እንዲጥሉ፣ እንዲሰበስቡና ለልማት እንዲጠቀሙ የሚያስችል ሕጋዊ ማዕቀፍ ይፈጥራል።

ይህም ፈጣን የከተሜነት መስፋፋትን ተከትሎ እያደገ የመጣውን የአገልግሎትና የመሠረተ ልማት ፍላጎት ለመመለስና የከተሞችን የፊስካል ነጻነት ለማረጋገጥ የተወሰደ ታሪካዊ እርምጃ መሆኑ ተመልክቷል።

በአዋጁ መሠረት “ንብረት” ተብለው የተለዩት በከተማ ቦታ ላይ የሚገኝ የሊዝ ይዞታ መብት፣ የነባር ይዞታ መጠቀሚያ መብት፣ ሕንፃ እና በቦታ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች ናቸው። ታክሱ በየዓመቱ የሚከፈል ሲሆን፣ የታክሱ መጠን እንደ ከተሞቹ ደረጃና እንደ ንብረቱ ዓይነት ይወሰናል። 

​በከተማ ቦታ የመጠቀም መብት ላይ የሚጣለው ታክስ ከንብረቱ ግምታዊ ዋጋ ከ0.2% ያላነሰ እና ከ1.0% ያልበለጠ እንዲሆን ተደንግጓል። በተጨማሪም ​ለልማት ተሰጥተው ነገር ግን በሕጉ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ሕንፃ ያልተገነባባቸው ወይም ጥቅም ላይ ያልዋሉ ቦታዎች ከፍተኛ ታክስ እንዲከፈልባቸው በማድረግ የመሬት ግምትን ለትርፍ የመጠቀም ተግባርን ለመከላከል ያለመ መሆኑ ካፒታል ጋዜጣ ተመልክቷል።

ክልሎች ይህንን ሞዴል አዋጅ ከየክልላቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም በምክር ቤቶቻቸው አፅድቀው ወደ ትግበራ እንዲገቡ ሚኒስቴሩ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

How To Use Cloud Storage Safely And Effectively

Cloud storage is now the default for many teams....

በኢትዮጵያ የሚገኘውን የኩርሙክ ወርቅ ማዕድን የሚያለማው አላይድ ጎልድ በ5.5 ቢሊዮን የካናዳ ዶላር ሊሸጥ ነው

በኢትዮጵያ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘውን ግዙፉን የኩርሙክ የወርቅ ማዕድን...

Zijin Gold to Acquire Allied Gold in C$5.5 Billion Cash Deal

In a move that highlights the intensifying wave of...

EXPRESSION OF INTEREST (EoI)

External Auditor for 2025 Organizational Audit Women Development and Reliance...

REQUEST FOR PROPOSALS FOR

Rebidding of Lot-5 and 6 of Rehabilitation and upgrading...

Invitation To Tender

For the supply of Supplementary Animal Feed Tender Reference -...

REQUEST FOR EXPRESSIONS OF INTEREST (REOI)

Country: Federal Democratic Republic of Ethiopia Client:National Bank of Ethiopia (NBE) Assignment...

Invitation to Bid for the Procurement of Contractors for Aluminium Cladding and Glazing Works

The Automotive Manufacturing Company of Ethiopia Share Company (AMCE)...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img