Monday, September 21, 2026

አይኤምኤፍ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 261 ሚሊዮን ዶላር እንዲለቀቅ ወሰነ

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በኢትዮጵያ እየተተገበረ ባለው የተራዘመ የብድር አቅርቦት ፕሮግራም ላይ አራተኛውን ግምገማ በማጠናቀቁ፤ አገሪቱ የ261 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ብድር እንድታገኝ መወሰኑን አስታወቀ።

ይህ ውሳኔ ኢትዮጵያ በፕሮግራሙ ሥር እስካሁን ያገኘችውን ጠቅላላ የገንዘብ መጠን ወደ 2.183 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ያደረገው ሲሆን፣ ገንዘቡ አገሪቱ የውጭ ክፍያ ሚዛንና የበጀት ፍላጎቶቿን እንድታሟላ ይረዳታል።

የድርጅቱ ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተር ናይጄል ክላርክ እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳው መሠረት እያከናወናቸው ያሉት ማሻሻያዎች ከሚጠበቀው በላይ ውጤት እያሳዩ ይገኛሉ።

በተለይም የውጭ ምንዛሬ ገበያውን ለማዘመን የተወሰዱ እርምጃዎች፣ የኤክስፖርት ዕድገት፣ የታክስ ገቢ አሰባሰብ መሻሻል እና የዋጋ ግሽበት መቀነስ ለኢኮኖሚው መረጋጋት ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መሆናቸውን ቦርዱ አረጋግጧል። ይሁን እንጂ ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣትና ድህነትን ለመቀነስ የማሻሻያ ሥራዎቹ በተመሳሳይ ፍጥነት መቀጠል እንዳለባቸው አሳስቧል።

ቦርዱ በውይይቱ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ገበያውን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግና የባንኮችን የተጣራ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ወደ ሕጋዊ ገደብ ለማምጣት እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ብሔራዊ ባንክ ከጨረታ ውጭ በውጭ ምንዛሬ ገበያው ውስጥ ጣልቃ እንዳይገባ የሚከለክል አዲስ መመሪያ መካተቱ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የበጀት ጉድለቱን ለመቆጣጠር፣ የታክስ መሠረቱን ለማስፋት እና የነዳጅ ድጎማን በሂደት ለማንሳት የገባውን ቃል ተግባራዊ ማድረጉ የበጀት ጥንካሬን ለመመለስ ወሳኝ መሆኑም በመግለጫው ተመልክቷል።

በመጨረሻም፣ ኢትዮጵያ ከብድር አበዳሪ አገራት (OCC) ጋር የደረሰችው የመግባቢያ ስምምነት አበረታች መሆኑን የጠቀሰው አይ ኤም ኤፍ፣ ከግል አበዳሪዎች ጋር የሚደረገው ድርድር ተጠናክሮ እንዲቀጥል መክሯል።

አገሪቱ አዳዲስ የንግድ ብድሮችን ከመውሰድ በመቆጠብና ቅድሚያ ለልማት ፕሮጀክቶች ትኩረት በመስጠት የብድር ጫናዋን እንድታቃልልም ድርጅቱ ጥሪ አቅርቧል።

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

አቶ ጀማል እና በላይነህ ክንዴ ከምርጫ ጋር ተያይዞ በፍርድቤት ክስ ተመሰረተባቸው

የሀገር አቀፍ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን የሚድሮክ...

Abel Birhanu

2. Education: (የት/ት ደረጃ)    10th 3. Company name: (የመስሪያ ቤቱ ስም)    Abel...

Ethiopia unveils 10-year master plan to transform date palm into major export crop

Ethiopia is orchestrating a structural transformation across its agricultural...

Africa at BRICS New Delhi: what it contributed and what it gained

The successful conclusion of the 18th BRICS Summit in...

Clearing the haze

Addis Ababa is confronting a severe environmental challenge, as...

Sub-Saharan Africa faces digital divide as handset costs and usage gap persist

While global mobile broadband networks continue to expand, Sub-Saharan...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img