Monday, June 8, 2026

በደረሰኝ እጥረት ምክንያት ይጣል የነበረው የ35 በመቶ የንግድ ትርፍ ግብር ውሳኔ ተቀየረ

​በኢትዮጵያ የሥጋ ኤክስፖርት ዘርፍ ውስጥ ለዓመታት እንቅፋት ሆኖ የቆየውና ላኪዎች ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮ የነበረው የታክስ አወሳሰን ሥርዓት መሠረታዊ ለውጥ እንደተደረገበት ተገልጿል።

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጡት አዲስ መመሪያ መሠረት፣ ቀደም ሲል የሥጋ ላኪዎች ከቁም እንስሳት አቅራቢዎች ጋር በሚያደርጉት ግብይት ላይ ሕጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ባለመቻላቸው ምክንያት ይጣልባቸው የነበረው የ35 በመቶ የንግድ ትርፍ ግብር ውሳኔ እንዲቀየር ተደርጓል። 

​በኢትዮጵያ የቁም እንስሳት አቅርቦት ዘመናዊ የግብይት ሥርዓትን ያልተከተለ በመሆኑ፣ ኤክስፖርት ቄራዎች እንስሳትን ከአርብቶ አደሮችና ከአነስተኛ አቅራቢዎች በሚገዙበት ወቅት ሕጋዊ ደረሰኝ ማግኘት ሲሳናቸው ቆይቷል።

ላኪዎቹ ግብይቱን በግዥ ማረጋገጫ ለመፈጸም ቢሞክሩም፣ አብዛኞቹ ሻጮች ለዚህ ፈቃደኛ ባለመሆናቸውና የታክስ ሕጉም በአንድ ሻጭ በዓመት ከ500 ሺህ ብር በላይ ግብይት ሲፈጸም ደረሰኝ ግዴታ መሆኑን በመደንገጉ፣ የታክስ ባለሥልጣኑ ላኪዎች ያወጡትን ወጪ ውድቅ ሲያደርግ ቆይቷል። 

​እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ላኪዎች ክፍያው በባንክ የተፈጸመ መሆኑን ቢያሳዩም፣ የታክስ ባለሥልጣኑ የወጪውን 65 በመቶ ብቻ በመቀበል፣ በቀሪው 35 በመቶ ላይ የንግድ ትርፍ ግብር ውሳኔ ያስተላልፍ ነበር። ይህ አሠራር ላኪዎች ሊከፍሉት የማይችሉት የታክስ ዕዳ ውስጥ እንዲዘፈቁና አንዳንዶቹም ከሥራቸው እንዲደናቀፉ ምክንያት ሆኖ መቆየቱን ካፒታል መዘገቡ ይታወሳል።

​ይህ ችግር ሀገሪቱ ከሥጋ ኤክስፖርት ልታገኝ የምትችለውን የውጭ ምንዛሪ በማዳከሙና አዳዲስ ገበያዎችን የማስፋፋት ሥራውን በማደናቀፉ፣ ብሔራዊ የኢንዱስትሪ ካውንስል ጉዳዩ ተጠንቶ መፍትሔ እንዲሰጠው አቅጣጫ አስቀምጧል።

በዚህም መሠረት ከገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከግብርና ሚኒስቴር እና ከጉምሩክ ኮሚሽን የተውጣጣ የጥናት ቡድን ተቋቁሞ ችግሩን መመርመሩ ተጠቁሟል።

​ጥናቱ እንደጠቆመው፣ ላኪዎች ላይ የሚጣለው 35 በመቶ የታክስ ዕዳ ኢንዱስትሪው ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ጫና ፈጥሯል። ይህንን ስጋት ለማቃለልም ጊዜያዊና ዘላቂ የመፍትሔ ሐሳቦች ቀርበው ጸድቀዋል።

​በገንዘብ ሚኒስቴር የተላለፈው ውሳኔ እንደሚያሳየው፣ የቁም እንስሳት አቅራቢዎች ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ተፈጻሚ እስኪሆን ድረስ አዲስ አሠራር ሥራ ላይ ውሏል። አዲሱ መመሪያ ላኪዎች ከአቅራቢዎች በሚፈጽሙት ግዥ ላይ የ3 በመቶ ቅድመ ግብር (Withholding Tax) ቀንሰው ለታክስ ባለሥልጣኑ ገቢ እንዲያደርጉ ያዝዛል። 

​ይህ የቅድመ ግብር አሠራር ቀደም ሲል በነበረው መመሪያ ቁጥር 2/2011 መሠረት ላኪዎች ላይ ተፈጻሚ ባይሆንም፣ አሁን ግን በዘርፉ የታየውን የደረሰኝ ችግር ለመፍታት ሲባል በልዩ ሁኔታ ተፈጻሚ እንዲሆን ተወስኗል።

በመመሪያው መሠረት ወጪው ተቀባይ እንዲሆን ለቁም እንስሳት አቅራቢው የተከፈለው ክፍያ በባንክ የተፈጸመ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ መቅረብ ያለበት ሲሆን፣ የግዥው መጠንና ዋጋም በግብርና ሚኒስቴር (በእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት) ተጠንቶ ከጸደቀው ስታንዳርድና ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ጋር መነጻጸር ይኖርበታል።

በተጨማሪም ምርቱ ወደ ውጭ ተልኮ የውጭ ምንዛሪ የተገኘበት መሆኑ መረጋገጥና አቅራቢውም የጸና የንግድ ፈቃድ ያለው ሊሆን ይገባል።

ይህ አሠራር እስከ አሁን የታክስ ውሳኔ ላልወጣባቸው ጉዳዮችና ወደፊት ዘመናዊ የግብይት ሥርዓት እስኪዘረጋ ድረስ እንደ ጊዜያዊ መፍትሔ የሚያገለግል ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ፣ ለመካከለኛና ለክልል የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ተሰራጭቶ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

ይሁን እንጂ ዘላቂ መፍትሔው በእንስሳት ዝርያዎች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የአቅርቦትና የዋጋ መረጃን በቴክኖሎጂ የታገዘ የማሰባሰብ ሥራ መሥራት መሆኑ ተጠቁሟል። አዲሱ መመሪያ በኤክስፖርት ቄራዎች ላይ የነበረውን የታክስ ስጋት በመቅረፍ ሀገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሪ ለማሳደግ ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል።

በኢያሱ ዘካሪያስ

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

SADC launches landmark initiative to build sustainable energy transition mineral value chains

The Southern African Development Community (SADC) region has many...

Kenya loses $92 million in AfDB shares after missing critical payment

Kenya has forfeited African Development Bank (AfDB) shares worth...

African island states seek stronger credit ratings for climate and blue economy finance

Experts, policymakers, and financial practitioners from across African Island...

IATA-ICAO deepen cooperation on boosting sustainable aviation fuels

The International Air Transport Association (IATA) and the International...

ITC, Equity group partner to unlock trade finance for coffee, leather and creative industries in East Africa

 (Nairobi/Geneva) – The International Trade Centre (ITC) and Equity...

Why Ethiopia should stop calling road crashes “Accidents”

The night of May 30, 2026 was an important...

Name:Rahel Nigussie

2 Education : ( የት/ት ደረጃ)103 Company Name (...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img