Sunday, September 20, 2026

የዩሮ ቦንድ የዕዳ ሽግሽግ ስምምነቱ ከአበዳሪዎች ኮሚቴ መመሪያ ጋር ባለመጣጣሙ እንዲቆም ተወሰነ

የገንዘብ ሚኒስቴር የሀገሪቱን የ1 ቢሊዮን ዶላር የዩሮ ቦንድ ዕዳ ለማዋቀር ከግል አበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር ደርሶት የነበረውን የመርህ ስምምነት ተግባራዊ እንደማያደርግ በይፋ አስታወቀ።

ጥር 2 ቀን 2026 ዓ.ም የተደረሰው ይህ ስምምነት እንዲቆም የተወሰነው፣ የመንግስታት አበዳሪዎች ኮሚቴ እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ስምምነቱን መርምረው ካጠናቀቁ በኋላ ነው።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ አሰንደገለፁት፤ የስምምነቱ መቋረጥ ዋነኛው ምክንያት “የአበዳሪዎች የእኩልነት መርህ”  ካለመከበሩ ጋር የተያያዘ ነው። የመንግስታት አበዳሪዎች ኮሚቴስምምነቱ ከሌሎች ይፋዊ አበዳሪዎች ጋር ከተደረገው የዕዳ ሽግሽግ ማዕቀፍ ጋር እንደማይጣጣም ለኢትዮጵያ መንግስት በደብዳቤ አሳውቋል።

ይህንን ስምምነት ባለበት ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ ሀገሪቱ በሐምሌ ወር 2025 ዓ.ም ከአበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር ከፈረመችው የመግባቢያ ሰነድ ጋር የሚቃረን ሆኖ ተገኝቷል።

በተጨማሪም፣ የተደረሰው ስምምነት ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ጋር ከገባችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ-ግብር ግቦች እና መለኪያዎች ጋር እንደማይጣጣም ተመልክቷል።

ሚኒስቴሩ እንዳለው ከሆነ፣ ስምምነቱን መቀጠል በሀገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት እና በተመዘገቡ የኢኮኖሚ እድገቶች ላይ ከፍተኛ ስጋት ሊፈጥር ስለሚችል በድጋሚ መደራደር የግድ ሆኗል።

በዚህም መሠረት፣ የኢትዮጵያ መንግስት የዕዳ ሽግሽጉን የፋይናንስ ይዘት በተመለከተ ከግል አበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር አዲስ ድርድር ለመጀመር መወሰኑን አስታውቋል።

መንግስት ውይይቱን በድጋሚ መክፈት አስፈላጊ ቢሆንም፣ በሁሉም አበዳሪዎች መካከል ፍትሃዊ የዕዳ ጫና ክፍፍልን የሚያረጋግጥ እና የሀገሪቱን የኢኮኖሚ አቅም ያገናዘበ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጿል።

Hot this week

Production up, but the ‘cost’ variable weighs heavily

Production is up in 2021 for the Italian agricultural...

Luminos Fund’s catch-up education programs in Ethiopia recognized

The Luminos Fund has been named a top 10...

Well-planned cities essential for a resilient future in Africa concludes the World Urban Forum

The World Urban Forum (WUF) concluded today with a...

Private sector deemed key to unlocking AfCFTA potential

The private sector’s role is vital to fully unlock...

Abel Birhanu

2. Education: (የት/ት ደረጃ)    10th 3. Company name: (የመስሪያ ቤቱ ስም)    Abel...

Ethiopia unveils 10-year master plan to transform date palm into major export crop

Ethiopia is orchestrating a structural transformation across its agricultural...

Africa at BRICS New Delhi: what it contributed and what it gained

The successful conclusion of the 18th BRICS Summit in...

Clearing the haze

Addis Ababa is confronting a severe environmental challenge, as...

Sub-Saharan Africa faces digital divide as handset costs and usage gap persist

While global mobile broadband networks continue to expand, Sub-Saharan...

El Niño drought threatens Ethiopian power supply to crypto miners

Ethiopian Electric Power (EEP) has confirmed that it may...
spot_img

Related Articles

Popular Categories

spot_imgspot_img